ፑቲን ምዕራባውያን ዩክሬን ሩሲያን በሚሳይል እንድትመታ በመፍቀድ "በእሳት እንዳይጫወቱ" አስጠነቀቁ
ፑተን ዩክሬን በምዕራባውያን ሚሳይሎች ሩሲያን የምታጠቃ ከሆነ አለምአቀፋዊ ግጭት ይቀሰቀሳል ብለዋል።
የሩሲያ ባለስጣናት ዩክሬን በሩሲያ ከተሞች እና የነዳጅ መሰረተልማቶች ላይ በምትፈጽማቸው ጥቃቶች ትግስታቸው እያለቀ መሆኑን እየተናገሩ ነው
ፑቲን ምዕራባውያን ዩክሬን ሩሲያን በሚሳይል እንድትመታ በመፍቀድ "በእሳት እንዳይጫወቱ" አስጠነቀቁ።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በአውሮፓ የሚገኙ የኔቶ አባላት ዩክሬን ከምዕራባውያን ባገኘችው መሳሪያ ተጠቅማ ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ ጥቃት እንድታደርስ በመፍቀድ በእሳት እንዳይጫወቱ ምዕራባውያንን በትናትናው አስጠንቅቀዋል።
ፑተን ዩክሬን በምዕራባውያን ሚሳይሎች ሩሲያን የምታጠቃ ከሆነ አለምአቀፋዊ ግጭት ይቀሰቀሳል ብለዋል።
ምዕራባውያን፣ ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ያለውን ግስጋሴ እንዴት እናስቁም የሚል ጭንቀት ውስጥ በገቡበት በዚህ ወቀት ፑቲን ግጭቱ ተስፋፍቶ አለምአቀፋዊ ሊሆን እንደሚችል አብዝተው በመናገር ላይ ናቸው።
የኔቶ ዋና ጸኃፊ ጀነራል ስቶልተንበርግ የኔቶ አባላት ዩክሬን በምዕራባውያን መሳሪያዎች ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ ጥቃት እንድትፈጽም ሊፈቅዱላት ይገባል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘ ኢኮኖሚስትን ጠቅሶ ዘግቧል።
"ቋሚ የሆነ ውጥረት አስከፊ የሆነ ውጤቶችን ያስከትላል" ሲሉ ፑቲን በታሽከንት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
"ይህ አስከፊ ውጤት በአውሮፓ የሚከሰት ከሆነ የእኛን የስትራቴጂክ ጦር መሳሪያ የበላይነት የምትገነዘበው አሜሪካ ምን ታደርጋለች? ይህን ለመናገር ከባድ ነው፤ አለምአቀፍ ግጭት ይፈልጋሉ?" ሲሉ ፑቲን ይጠይቃሉ።
ፕሬዝደንት ፑቲን ዩክሬን በሩሲያ ምድር ላይ ልታደርስ የምትችለው የረጅም ርቀት ሚሳይል ጥቃት የምዕራባውያን የሳተላይት፣ የስለላ እና ወታደራዊ እርዳታ ስታገኝ ነው፤ ስለዚህ ምዕራባውያን በቀጥታ ተሳታፊ ይሆናሉ ማለት ነው ብለዋል።
ፑቲን በአውሮፓ የሚገኙ ውስን ስፋት እና የተጠጋጋ ህዝብ የሰፈረባቸው ትናንሽ ሀገራት"በምን እየተጫወቱ እንዳሉ ማወቅ አለባቸው" ሲሉ ተናግረዋል።
"ይህ ወደ ሩሲያ ዘልቀው ጥቃት ከመሰንዘራቸው በፊት ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው"ብለዋል ፑቲን።
ሩሲያ በ2022 በዩክሬን ላይ የከፈተችው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ከምዕራባውያን ጋር ያላትን ግንኙነት በ60 አመታት ውስጥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ አድርሶታል።
የምዕራባውያን ሀገራት መሪዎች እና ዩክሬን ከአለም ግዙፍ የኑክሌር ጦር መሳሪያ በታጠቀችው ሩሲያ እና በአለም ትልቁ በሆነው የኔቶ ወታደራዊ ጥምረት መካከል ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለውን የሩሲያን ማስጠንቀቂያ እያጣጣሉት ነው።
ዩክሬን፣ ሩሲያ ከግዛቷ ማስወጣት እና በሩሲያ ምድርም ጥቃት መፈጸም እንደምትችል እየገለጸች ትገኛለች።
ነገርገን የሩሲያ ባለስጣናት ዩክሬን በሩሲያ ከተሞች እና የነዳጅ መሰረተልማቶች ላይ በምትፈጽማቸው ጥቃቶች ትግስታቸው እያለቀ መሆኑን እየተናገሩ ነው።
18 በመቶ የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት የተቆጣጠረችው ሩሲያ አሁንም ማጥቃቷን ቀጥላለች።