ፑቲን ደቡብ ኮሪያ "ትልቅ ስህተት እየሰራች ነው” ሲሉ አስጠነቀቁ
ደቡብ ኮሪያ የሩሲያና ሰሜን ኮሪያ ስምምነትን ተከትሎ ለዩክሬን መሳሪያ እሰጣለሁ ብላለች
ፑቲን “ሴኡል ለኪየቭ የጦር መሳሪያ ካቀረበች ሞስኮ የደቡብ ኮሪያን አመራርን ሊያስቀይም የሚችል ውሳኔ ትወስናለች” ብለዋል
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደቡብ ኮሪያ ዩክሬንን ለማስታጠቅ ማሰቧ ትልቅ ስህተት ነው ሲሉ ገለጹ።
ሰሜሪ ኮሪያ እና ሩሲያ ከሁለቱ በአንደኛቸው ላይ ወታራዊ ጥቃት በሚቃጣበት ወቅት ወታራዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሀገራቱ መሪዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወቃል።
- ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ አንዳቸው ለሌላኛቸው ሁሉንም አይነት ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደረሱ
- ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ስምምነት ላይ የደረሱባቸው ቁልፍ የትብብር ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?
ደቡብ ኮሪያ የሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ አዲስ የስምምነት ማእቀፍን ተከትሎ ዩክሬንን ልታስታጥቅ እንደምትችል እንደምትችል ገልጻለች።
ፑቲን ይህንን ተከትሎ በሰጡት አስተያየትዩክሬን በከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ላይ ደቡብ ኮሪያ ለኪቭ መሳሪያ ለማቅረብ በማሰቧ ትልቅ ስህተት እየሰራች ነው ብለዋል።
ሴኡል ለኪየቭ የጦር መሳሪያ ለማቅረብ ከወሰነች ሞስኮ “አሁን ያለውን የደቡብ ኮሪያን አመራር ሊያስቀይም የሚችል ውሳኔ ትወስናለች” ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አክለውም አሜሪካ እና አጋሮቿ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ማቅረብ ከቀጠሉ ሞስኮ ፒዮንግያንግን ለማስታጠቅ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
“የጦር መሳሪያዎች ለዩክሬን የሚያቀርቡ አካላት ከእኛ ጋር ጦርነት ውስጥ እንዳልሆኑ ያምናሉ” ያሉት ፑቲን፤ እኛ ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ ለሌሎች የአለም ሀገራት የጦር መሳሪያ የማቅረብ መብታችን የተጠበቀ ነው” ብለዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከ24 ዓመታት በኋላ በሰሜን ኮሪያ ያደረጉት ጉብኝት እና አዲስ ስምምነት ደቡብ ኮሪያን አበሳጭቷል።
ፑቲን በፒዮንግያንግ ቆይታቸው፤ ሰሜሪ ኮሪያ እና ሩሲያ ከሁለቱ በአንደኛቸው ላይ ወታራዊ ጥቃት በሚቃጣበት ወቅት ወታራዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሀገራቱ መሪዎች ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
"ኮምፕሬሄንሲቭ ስትራቴጂክ ፓርትነርሺፕ" ለማድረግ በሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን እና በሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን መካከል የተደረሰው ስምምነት ሞስኮ በአመታት ውስጥ በእስያ አህጉር ያደረገችው ትልቅ እርምጃ ነው።
"ከሁለቱ በአንደኛቸው ላይ ጦርነት የሚታወጅ ከሆነ ወይም በጦርነት ውስጥ ካለ፣ በተመድ ቻርተር አንቀጽ 54 መሰረት ሌላኛው ሁሉንም አይነት ወታራዊ እና ሌሎች ድጋፎችን ወዲያውኑ ያቀርባል" ይላል የስምምነቱ አንቀጽ አራት።
ስምምነቱ ሩሲያ በዚህ ምዕተ አመት የኑክሌር ጦር መሳሪያ የሞከረችውን ሰሜን ኮሪያን ምን ያህል ልትረዳት ትችላለች የሚል ምዕራባውያንን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል።