ሞስኮ ከተመራጩ ፕሬዝዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ለተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አልዎት መልእክት አስተላልፈዋል።
ከምርጫው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት የሰጡት ፑቲን፤ በሶቺ ቫልዳይ ጉባዔ ላይ ንግግር ሲያደርጉም “ትራምፕ ደፋር ሰዉ ነዉ” ሲሉም አሞከሽተዋቸዋል።
ፑቲን ትራምፕ በሐምሌ ወር በፔንስልቬንያ በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ንግግር ሲያደርጉ የግድያ ሙከራ በተደረገባቸው ወቀት የደፋር ሰው ተግበር ፈጽመዋል ሲሉም አድንቀዋል።
ፑቲን ስለ ግድያ ሙከራው ሲያወሩም “በእኔ አስተያየት ትራምፕ በወቅቱ በጣም ትክክለኛ በሆነ እና ድፍረት በተሞለበት መንገድ ተመንቀሳቅሷል”ብለዋል።
ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ስለ ዩክሬን ያነሱት እና ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ የሰጡት አስተያየት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል ፑቲን በንግገራቸው።
ትራምፕ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን ጦርነት "በአንድ ቀን" ማቆም እንደሚችሉ ደጋግመው ተናግረዋል እንዴት ተብሎ ሲጠየቁ ድርድሮችን ተግባራዊ በማድረግ ከማለት በቀር ዝርዝር አተገባበሮችን ገልጸው አያውቁም፡፡
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም “አሁን ምን እንደሚሆን አላውቅም፣ ምንም ፍንጭ የለኝም” ሲሉም ተናግረዋል።
ፑቲን አክለውም፤ የትራምፕ አስተዳደር ከፈለገ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን እና ከትራምፕ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።