ፑቲኔ የዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከሽፏል ብለዋል
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "ልዩ ተልዕኮ" ያሉት ጦርነት ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል በመገንዘብ ሁኔታውን አምነው እንደተቀበሉት አመልክተዋል።
ኪየቭ የተኩስ አቁም ስምምነቶችን ጦሯን ዳግም ለማስታጠቅ ልትጠቀምበት ትችላለችም ብለዋል።
የዋሽንግተንን የቀጣይ ዓመት ምርጫ ማንም አሸነፈ ማን ሀገሪቱ ሞስኮን እንደ ጠላቷ ማየቷ አያበቃም ሲሉም አዲስ ነገር እንደማይኖር ጠቁመዋል።
በምስራቅ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለሰዓታት የተናገሩት ፑቲን፤ የዩክሬን መልሶ ማጥቃት ዘመቻ እስካሁን ከሽፏል ብለዋል።
ኪየቭ በጥቃቶቿ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ 71 ሽህ ወታደሮችን አጥታለችም ሲሉ ተደምጠዋል።
ዩክሬን ወታደር፣ ትጥቅና ጥይት ስታጣ ስለ ሰላም ታወራለች ሲሉም ኪየቭ ለእውነተኛ የሰላም ንግግር ፍላጎት እንደሌላት ጠቁመዋል።
ሀገሪቱ የግጭት ማቆም አፍታ ስታገኝ ጦሯን ለማደራጀት ትጠቀምበታለች ሲሉ ኪሳራው እንደሚያመዝን ተናግረዋል።
ጉምቱ አሸማጋዮች ሩሲያ ጦርነቱን ለማቆም ዝግጁ ስለመሆኗ ጠይቀዋል ያሉት ፑቲን፤ የዩክሬን መልሶ ማጥቃት እያለ ሞስኮ በፍጹም አይቃጣትም ብለዋል።
የሰላም ንግግር ከተፈለገ ዩክሬን ድርድር ላይ የጣለችውን እግድ አንስታ "ምን እንደምትፈልግ" ታብራራ ሲሉ ተደምጠዋል።
ሩሲያ 18 በመቶ የዩክሬንን ግዛት ተቆጣጥራለች።ፑቲኔ የዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከሽፏል ብለዋል