ፑቲን በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያቸውን የውጭ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
ፑቲን ወደ ከጉብኝቱ መርሃግብር በፊት የካቢኔ አባላት ሸግሽግን አጠናቀዋል
ክሬሚሊን እንደገለጸው ፕሬዝደንን ፑቲን በፕሬዝደንት ሺ ግብዣ በዚህ ሳምንት በቻይና ጉብኝት ያደርጋሉ
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ ዙር የስልጣን ዘመን በዓለ ሲመታቸውን ከፈጸሙ በኋላ የመጀመሪያ የውጭ ጉብኝታቸውን በዚህ ሳምንት በቻይና ሊያደርጉ መሆኑን ክሬሚሊን አስታውቋል።
ፑቲን ወደ ከጉብኝቱ መርሃግብር በፊት የካቢኔ አባላት ሽግሽግን አጠናቀዋል።
ፑቲን ባካሄዱት የካቢኔ ሽግሽግ በሁለት አመቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሰሬጌ ሾይጉ ወደ ሌላ ኃላፊነት ሲያዛወሩ፣ ሌሎቹ ባሉበት ቀጥለዋል።
ፑቲን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው በእጩነት ያቀረባቸው አንዴሬ ቤሎሼቭ በሙያ ኢኮኖስት ናቸው።
"ቭላድሚር ፑቲን በፕሬዝዳንት ሺ ግብዣ ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ የመጀመሪያ የውጭ ጉብኝታቸውን ከግንቦት16-17 በቻይና ያካሄዳሉ" ብሏል ክሬሚሊን።
ክሬሚሊን እንደገለጸው ፑቲን እና ሺ "ትብብር በሚደረግባቸው ጉዳዮች እና በስትራቴጂክ ግንኙነት ዙሪያ እንዲሁም አንገብጋቢ በተባሉ ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ"።
መሪዎቹ ከውይይታቸው በኋላ የጋራ መግለጫ ያወጣሉ ተብሏል።
የእስያ ሀያላን የሆኑት ሩሲያ እና ቻይና፣ የምዕራባውያን ተቀናቃኝ የሆነው በማድግ ላይ ያሉ ሀገራትን በአባልነት ያቀፈው ብሪክስ የተባለው ጥምረት መስራች ናቸው።
ሀገራቱ የአሜሪካ ዶላር ከገበያ እንዲወጣ እና አማራጭ ገንዘብ ጥቅም ላይ እንዳውል ይፈልጋሉ።
ምዕራባውያን፣ ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለውን ጦርነት እንድታወግዝ እና ከዚህም አልፋ በፕሬዝደንት ፑቲን ላይ ጫና እንድታሳድር ቻይናን በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። ነገርግን ቻይና ሰላማዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ከመግለጿ ውጭ በቀጥታ ሩሲያን ስታወግዝ አልታየችም።