"ለእናንተ መናገር የምፈልገው እኔ የብራዚል ፕሬዝደንት ሆኜ፣ ፑቲን ወደ ብራዚል ከመጣ የሚታሰርበት መንገድ የለም።" ብለዋል ሉላ
ፑቲን በሚቀጥለው አመት በብራዚል ሪዮ ዲጀነሪዮ በሚካሄደው የቡድን20 ጉባዔ የሚካፈሉ ከሆነ እንደማይታሰሩ ተናግረዋል።
ሉላ በህንድ በተካሄደው የዘንድሮ የቡድን20 ጉባኔ ላይ እንደገለጹት ፑቲን በቡድን20 አባል ሀገራት ጉባዔ ላይ እንዲካፈሉ እንደሚጋበዚ እና ከሪዮ ስብሰባ በፊት በሩሲያ በሚካሄደው የብሪክስ የአዳጊ ሀገሮች ጉባዔ ለመካፈል አቅደዋል።
"ፑቲን በቀላሉወደ ብራዚል ይሄዳል ብየ አስባለሁ።"
"ለእናንተ መናገር የምፈልገው እኔ የብራዚል ፕሬዝደንት ሆኜ፣ ፑቲን ወደ ብራዚል ከመጣ የሚታሰርበት መንገድ የለም።" ብለዋል ሉላ።
ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት ፑቲን የዩክሬንን ህጻናት በህወጥ መንገድ በማስወጣት የጦር ወንደል ፈጽመዋል በሚል የመያዧ ትዕዛዝ ማውጣቱ ይታወሳል።
ፑቲን በተደጋጋሚ አለምአቀፍ ስብሰባችን አልተካፈሉም። በቅርቡ በህንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው የቡድን20 ሀገራት ጉባዔ ላይ አልተሳተፉም።
ብራዚል የፍርድ ቤቱ አባል መሆኗ ኦና አሳልፋ የመስጠት ግዴታ ቢኖርባትም፣ ፑቲንን አሳልፋ እንደማትሰጥ ገልጻለች።