ለኑክሌር ጦርነት ዝግጁ ነን ሲሉ ፑቲን ምዕራባውያንን አስጠነቀቁ
ፑቲን አሜሪካ ወደ ዩክሬን ወታደሮቿን የምትልክ ከሆነ ጦርነት ከፍተኛ መካረር ላይ ይደርሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ለኑክሌር ጦርነት መዘጋጀቷን ተናግረዋል
ለኑክሌር ጦርነት ዝግጁ ነን ሲሉ ፑቲን ምዕራባውያንን አስጠነቀቁ።
ሩሲያ ለኑክሌር ጦርነት መዘጋጀቷን የገለጹት የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ ወደ ዩክሬን ወታደሮቿን የምትልክ ከሆነ ጦርነት ከፍተኛ መካረር ላይ ይደርሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ፑቲን ተጨማሪ የስድስት አመት ያስገኝላቸዋል ከተባለው የመጋቢቱ ምርጫ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት በሰጡት በዚህ ቃለምልልስ የኑክሌር ጦርነት እንደማያስቸኩል እና በዩክሬን የኑክርሌር መሳሪያ መጠቀም አስፈላጊት እንዳልታያቸው ተናግረዋል።
"በርግጥ ከወታደራዊ ቴክኒክ አንጻር ካየነው፣ ዝግጁ ነን" ሲሉ ፑቲን ለሩሲያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ሪያ ተናግረዋል።
አሜሪካ ወደ ዩክሬን ወታደሮቿን የምትልክ ከሆነ ሩሲያ እንደጣልቃገብነት እንደምትቆጥረው ተረድታለች ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን አክለውም "(በአሜሪካ ውስጥ) እዚያ በአሜሪካ እና ሩሲያ ግንኙነት እና ስትራቴጅካዊ ተአቅቦ በማድረግ ዙሪያ በቂ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች አሉ" ብለዋል።
"ስለሆነም ለኑክሌር ፍጥጫ መቸኮሎ አለብን ብዬ አላስብም፣ ነገርግን እኛ ዝግጁ ነን"
በዩክሬን የተጀመረው ጦርነት ከ1962ቱ የኩባ የሚሳይል ቀውስ ወዲህ በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ከፍተኛ የተባለ ፍጥጫን ፈጥሯል። ፑቲንም ምዕራባውያን ጦር ወደ ዩክሬን የሚልኩ ከሆነ የኑክሌር ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል በተደጋሚ አስጠንቅቀዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከከፈተች ሁለት አመት ያስቆጠረ ሲሆን ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
በቅርቡ የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን ባደረገው ጦርነት ወሳኝ የተባለችው አቭዲቪካን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን በመቆጣጠር ባለው ሰኔ ወር ባክሙትን ከተቆጣጠረ ወዲህ ከፍተኛ የሚባል ድል አስመዝግቧል።
ዩክሬን እነዚህን ከተሞች ለመልቀቅ የተገደደችው የምዕራባውያን ወታደራዊ ድጋፍ ቶሎ ባለመድረሱ እና ወታደሮቿ ከበባ ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ መሆኑን ገልጻለች።