ሴራ ኔቫዳ ኮርፖሬሽን የተሰኘው ተቋም ይህን ግዙፍ አውሮፕላን ለመስራት ተስማምቷል
አሜሪካ ለዓለም ፍጻሜ መሸሸጊያ የሚውል አውሮፕላን እንዲሰራ አዘዘች፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ እንደ ኑክሌር አይነት ጦርነት ቢነሳ ከአደጋ መጠበቅ የሚቻልበት አውሮፕላን እንዲሰራ ማዘዟ ተገልጿል፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ አሜሪካ በ1970ዎቹ የተሰራ የክፉ ቀን መጠለያ አውሮፕላን የሰራች ሲሆን ይህ አውሮፕላን አርጅቷል በሚል አዲስ ልዩ አውሮፕላን እንዲሰራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ለክፉ ቀን ማምለጫ ይሆናል የተባለው ይህ አውሮፕላንም 13 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይፈጃል የተባለ ሲሆን ሴራ ኔቫዳ ኮርፖሬሽን የተሰኘው ኩባንያ አዲሱን አውሮፕላን እንደሚሰራው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሶማሊያ ስንቅ ሰርቀዋል ያለቻቸውን በአሜሪካ የሰለጠኑ ኮማንዶዎቿን አሰረች
ኢ-4ቢ የተሰኘ ስያሜ ያለው ይህ አዲስ አውሮፕላን አውሮፕላን በፈረንጆቹ 2036 ላይ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ አየር ሀይል ንብረት የሆነው ይህ ልዩ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ይዟል ተብሏል፡፡
እንዲሁም አውሮፕላኑ እንደ ኑክሌር ጦርነት፣ አውዳሚ አደጋዎች እና ሌሎች አስጊ ክስተቶች ቢከሰቱ መሪዎች በዚህ አውሮፕላን ላይ በመሆን ትዕዛዝ እና ውሳኔዎችን እንዲያካሂዱ ያገለግላልም ተብሏል፡፡
የመሰብሰቢያ ቢሮዎች፣ የነዳጅ መሙያዎች እና የተግባቦት መሳሪያዎችም ያሉት ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለው የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን ከ2030 በኋላ ከአገልግሎት ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡