ባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኪዩመንን በውጤት ማጣት ምክንያት ከክለቡ መሰናበቱ ይታወሳል
የኳታሩን አልሳድ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኙ ዣቪ ሄርናንዴዝን ለመልቀቅ መስማማቱ ተስመቷል።
ከፈረንጆቹ 1998 እስከ 2015 ዓመት ድረስ በባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ በመሀል ተጫዋችነት ያገለገለው ስፔናዊ የኳስ አቀጣጣይ ዣቪ ሄርናንዴዝ አሁን ላይ የኳታሩን አልሳድ እግር ኳስ ክለብን በማሰልጠን ላይ ይገኛል።
ባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኪዩመንን በውጤት ማጣት ምክንያት ከክለቡ መሰናበቱ ይታወሳል።
የኪዩመንን ስንብት ተከትሎም ባርሴሎና የቀድሞ ተጫዋቹን በአሰልጣኝነት ለመቅጠር ከዥቪ እና ከክለቡ ጋር ላለፉት ቀናት ሲደራደር ቆይቷል።
አልሳድ እግር ኳስ ክለብ እንዳሳወቀው ከባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ ጋር ዣቪን ለመልቀቅ መስማማቱን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ዣቪ በትናንትናው ዕለት እንደተናገረው “ወደ ባርሴሎና ክለብ መሄድ እፈልጋለሁ ወደ ባርሴሎና መመለስ ህልሜ ነው” ብሏል።
ዣቪ በባርሴሎና በቆየባቸው 17 ዓመታት 779 ጨዋታዎችን በማድረግ 25 ዋንጫዎችን ማሸነፉ ይታወሳል።