ልዩልዩ
የጋዜጠኛ አስፋውን ህይወት ለማትረፍ 200ሺ ዶላር መሰብሰብ ተችሎ ነበር
ጋዜጠኛ አስፋው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ነው ህይወቱ ያለፈው
ተወዳጁ የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢና አዘጋጅ በበጎ ስራዎቹም ይታወቃል
ጋዜጠኛ አስፋው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቀይቶ ህይወቱ ማለፉን ኢቢኤስ እና የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የጋዜጠኛ አስፋው ልጅ ሳምሶን መሸሻ ወይ ጃፒ፣ አባቱ የስትሮክ ህመም እንዳጋጠመው እና ለህክምና የሚሆን እርዳታ እንደሚፈልግ "በጎ ፈንድ ሚ" መግለጫው ላይ አስፍሮ ነበር።
ጥሪውን ተከትሎ በሳምሶን ስም በተከፈተው "የጎፈንድ ሚ አካውንት" 202,331 የአሜሪካን ዶላር ተሰብሰቧል።
ሳምሶን ጋዜጠኛ አስፋው በአሜሪካን ሀገር ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እየታከመ እንደሚገኝም ገልጾ ነበር።
ከሁለት ሳምንት በፊት ሳምሶን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ቀርቦ ከ200ሺ ዶላር በላይ መሰብሰቡን እና እርዳታውን ላደረጉት የጋዜጠኛው አድናቂዎች እና ወዳጆች ምስጋና አቅርቧል።
ተወዳጁ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ በኤፍኤም አዲስ 97.1 “አይሬ” በተባለ የሙዚቃ ፕሮግራሙ ይታወቅ ነበር።
በኢቢኤስ ቴሌቪዥንም “ኑሮ በአሜሪካ” በተሰኘ ፕሮግራሙ ተወዳጅ የነበረው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በህመም አልጋ ላይ እስኪወድቅ ድረስ በቴሌቪዥን ጣቢያው በፕሮግራም አቅራቢነት ሲያገለግል ቆይቷል።