የረመዳን ጾም በረከት ከመንፈሳዊ ጥቅሙ ባሻገር
የረመዳን ጾም ከተጀመረ 10ኛ ቀኑ ላይ ይገኛል

የዕምነቱ ተከታዮች ይህን የጾም ወቅት ከፈጣሪያው ጋር ከመገናኘት ባለፈ ክብደት ለመቀነስ እና አመጋገባቸውን ለማስተካከልም ይጥቀሙበታል
በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የረመዳን ጾም ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡
ጤነኛ የሆኑ የእስልምና ዕምነት አማኞች በሙሉ ይጾሙታል የሚባለው ይህ የረመዳን ወር የእስልምና ዕምነት ካሉት አምስት ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው፡፡
የካቲት 22 ቀን የተጀመረው የዘንድሮው የረመዳን የጾም 10ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ጾም ሰዎች ከፈጣያቸው ጋር የበለጠ ከማቀራረቡ በተጨማሪ ሌሎች የጤና ጥቅሞች አሉት፡፡
ሰውነታችን በጾም ወቅት ለረጅም ሰዓት ያለ ምግብ ስለሚቆይ በሰውነታችን ውስጥ የተከማቹ ስቦች እንዲቀልጡ እና የተስተካከለ ሰውነት እንዲኖርም ይረዳል፡፡
አል አረቢያ ከታዋቂዋ የስነ ምግብ ሐኪም ከሆኑት ዶክተር ሞና ጁማ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ የረመዳን የጾም ወቅት ከመንፈሳዊ አገልግሎቱ ባለፈ አመጋገብን ለማስተካከል እና የሰውነት ክብደት ለመቀነስ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡
በተለይም የሰውነታቸው ክብደት የጨመረባቸው ጿሚዎች የሚመገቡትን ምግብ በማመጣጠን፣ ከጾም በኋላም እንዲቀጥል የሚያደርግ አመጋገብ ቢከተሉ ሲሉም ዶክተር ሞና ምክረ ሀሳባቸውን ለግሰዋል፡፡
ለረጅም ሰዓት ያለ መግብ መቆየት በራሱ ክብደት እንድንቀንስ ይረዳል የሚሉት ዶካተር ሙና በኢፍጣር ወቅት በረሃብ ምክንያት ብዙ ምግብ ከመመገብ መቆጠብ እና ጣፋጭ ምግቦችን በመቀነስ አልያም በማስወገድ ክብደት መቀነስ ይቻላልም ተብሏል፡፡
የሰውነታችን የስኳር መጠን ለማመጣጠን ሲባልም በተፈጥሯቸው አነስተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦች መመገብ፣ የተቀነባበሩ ምግብችን ማስወገድ እና መሰል እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ይሁንና ይህ የአመጋገብ ስልት ከረመዳን ጾም በኋላም ካልቀጠለ ዳግም ተጨማሪ የሰውነት ክብደት እንዲፈጠር ሊያደርግ ስለሚችል ዘላቂ እና ጤናማ የሚባል አመጋገብን መከተል እንደሚገባም ባለሙያዋ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡