በረመዳን ጾም ወቅት ማድረግ ያሉብን የጤና ምክረ ሀሳቦች ምን ምን ናቸው?
የዘንድሮው የረመዳን ወር ነገ ይጀመራል

ለአንድ ወር የሚቆየው የረመዳን ጾም ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው
በረመዳን ጾም ወቅት ማድረግ ያሉብን የጤና ምክረ ሀሳቦች ምን ምን ናቸው?
በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የረመዳን ጾም ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡
ጤነኛ የሆኑ የእስልምና ዕምነት አማኞች በሙሉ ይጾሙታል የሚባለው ይህ የረመዳን ወር የእስልምና ዕምነት ካሉት አምስት ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው፡፡
አማኞችን ከፈጣሪያቸው ጋር የበለጠ ያቀራርባል በሚባለው በዚህ ጾም ወቅት ሀገራት ለዜጎቻቸው የስራ ጫና እንዳይበዛባቸው የሚያደርጉበትም ነው፡፡
የስነ ምግብ ባለሙያዋ ዶክተር ላማ ዳሉል በዚህ የጾም ወቅት ከጤና አንጻር ጿሚዎች ቢከተሏቸው ያሏቸውን ምክረ ሀሳብ ለግሰዋል፡፡
እንደ ዶክተር ላማ ምክረ ሀሳብ ከሆነ ጿሚዎች በጾም ወቅት ከባድ የሚባሉ የሰወነት እንቅስቃሴዎችን እንዳያደርጉ የመከሩ ሲሆን ከባድ ድካም ለሌሎች የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል ብለዋል፡፡
ከኢፍጣር በኋላ ሰውነታችን በቂ ፈሳሽ እንዲያገኝ ቀስ በቀስ እስከ 10 ብርጭቆ ድረስ እንዲጠጡ መከራል የሚሉት ባለሙያዋ ለስላሳ እና ጣፋጮጭ መጠጦችን ማብዛት ሰውነታችን በቂ ውሃ እንዳያገኝ እንደሚያደርገውም አክለዋል፡፡
ሌላኛው ለጿሚዎች የቀረበው ምክረ ሀሳብ በተቻለ መጠን ሰውነታችን በቂ ንጥረ ነገር እንዲያገኝ የተመጣጠነ እና አይነተ ብዙ አመጋገቦችን መከተል የተሻለ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡
በጾም ወቅት በተለይም ለሰውነታችን ሚዛን ጠቃሚ የሆኑ እንደ ማግኒዢየም፣ ሶዲየም እና በቫይታሚኖች የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ እንደሚገባም ባለሙያዋ ከአል አረቢያ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ላይ ተናግረዋል፡፡