1446ኛው የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል
በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጨረቃ ክትትል ኮሚቴ የረመዳን ወር ጨረቃ ዛሬ መታየቷን አስታውቋል

ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት ውስጥ አንዱ ነው
የረመዳን ጾም ነገ ቅዳሜ እንደሚጀመር ተገለጸ።
በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጨረቃ ክትትል ኮሚቴ የረመዳን ወር ጨረቃ ዛሬ በተሟላ መልኩ መታየቷን አስታውቋል።
ረመዳን በሂጅራ አቆጣጠር ዘጠነኛው ወር የሚውል ሲሆን በሙስሊሞች ዘንድ የጾምና ጸሎት ወር ነው።
ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ጾሙ ለሃያ ዘጠኝ ወይም ሰላሳ ቀናት ይቆያል።
የረመዳን ወር የመረዳዳት፣ የመተጋገዝና የመከባበሪያ ወር ነው።
ሙስሊሙ ማህበረሰብም ፈጣሪ የሚወደውን በጎ ተግባራት በማከናወን ጾሙን እንዲያሳልፍ የእምነቱ አስተምህሮ ያዛል።