በሱዳን በጦርነቱ ምክንያት አስገድዶ መድፈር በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተባለ
በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ባለፈው ሚያዚያ ወር ነበር
ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሴቶች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ተዋጊ ኃይሎች ካሉ ይጠየቃሉ ሲል ለቀረበበት ክስ ምላሽ ሰጥቷል
በሱዳን በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት አስገድዶ መድፈር እና ጠለፋ በአሳሳቢ ሁኔቴ እየጨመረ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶቾ ተናግረዋል።
በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የተጀመረው ጦርነት የ12 አመት እድሜ ካላቸው ሴቶች ጀምሮ ተጠለፋ እንዲካሄድባቸው ምክንያት መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች እና ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የህጻናት አድን ጅርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) ሴቶች ልጆች በተዋጊ ኃይሎች እየተደፈሩ መሆናቸውን ሲገልጽ፣ተመድ በበኩሉ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየጨመረ ነው ብሏል።
በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ባለፈው ሚያዚያ ወር ነበር።
ጦርነቱ በዋናነት እየተካሄደ ያለው በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እና በምዕራብ ዳርፉር ግዛት ነው።
የሱዳን መንግስት ኮምባቲንግ ቫዮለንስ አጌኒስት ውሜን(ሲቪኤደብሊው) እንደገለጸው ሴቶች ለበርካታ ቀናት ተጠልፈው ፆታዊ ጥቃት እየተፈጸመባቸው እና በቡድን እየተደፈሩ መሆኑን ገልጿል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሴቶች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ተዋጊ ኃይሎች ካሉ ይጠየቃሉ ሲል ለቀረበበት ክስ ምላሽ ሰጥቷል።
ተመድ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ 4.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ለጥቃት ተጋላጭ ናቸው የሚል ግምት አስቀምጧል።