ሪያል ማድሪድ በአመት ከ1 ቢሊየን ዩሮ በላይ ገቢ በማግኘት የመጀመሪያው ክለብ ሆነ
የሻምፒዮንስ ሊግ እና ላሊጋ ዋንጫን ያሳካው የስፔኑ ክለብ ባለፈው የውድድር አመት 1.045 ቢሊየን ዩሮ ማግኘቱን ዴሎይት አስታውቋል
የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እስከ 20ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረውታል
ሪያል ማድሪድ በአመት ከ1 ቢሊየን ዶላር ዩሮ ገቢ በማስገባት የመጀመሪያው ክለብ ሆነ።
ዴሎይት የተባለ ድርጅት ባወጣው አመታዊ ሪፖርት የስፔኑ ክለብ በ203/24 የውድድር አመት 1.045 ቢሊየን ዩሮ አግኝቷል።
ይህም የሻምፒዮንስ ሊግ እና ላሊጋ ዋንጫ ያነሳውን ማድሪድ በአንድ አመት ውስጥ ከ1 ቢሊየን ዩሮ በላይ ወደካዝናው ያስገባ የመጀመሪያው ክለብ ያደርገዋል ተብሏል።
የስፔኑ ክለብ በርናባው ስታዲየምን ካሳደሰ በኋላ የስታዲየም ገቢው በእጥፍ አድጎ 248 ሚሊየን ዶላር ማግኘቱን የዴሎይት መረጃ ያሳያል።
ከመለያ ስፖንሰሮች የሚያገኘው ገቢም በ19 በመቶ አድጎ በባለፈው የውድድር አመት 482 ሚሊየን ዩሮ አስገብቷል ነው የተባለው።
በማድሪድ በተከታታይ ደረጃውን የተነጠቀው የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ 837 ሚሊየን ዩሮ (707 ሚሊየን ፓውንድ) በማስገባት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ የገባው ብቸኛው የፈፈረንሳይ ክለብ ፒኤስጂ በ680 ሚሊየን ፓውንድ ሶስተኛ ላይ ተቀምጧል።
ማንቸስተር ዩናይትድ ምንም እንኳን ባለፈው አመት በፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ደረጃን ይዞ ቢያጠናቅቅም 650 ሚሊየን ፓውንድ በማስገባት አራተኛ ደረጃን ሲይዝ ባየርሙኒክ እና ባርሴሎና ይከተላሉ።
አርሰናል በበኩሉ በ605 ሚሊየን ፓውንድ ገቢ ሰበተኛ ደረጃን መያዙን ያስታወቀው ዴይሎት፥ ሊቨርፑል ከመድፈኞቹ በ2 ሚሊየን ፓውንድ ዝቅ ብሎ ሰምንተኛ መሆኑን ጠቁሟል።
ቶተንሃም ሆትስፐር እና ቼልሲ እስከ 10ኛ ደረጃን የያዙ ሲሆን፥ የእንግሊዝ ክለቦች በአመታዊ ገቢ ደረጃው እስከ 20ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረውታል።
ለክለቦች ገቢ በአውሮፓ መድረክ ውድድሮች መሳተፍ ትልቅ ድርሻ አለው።
የጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ከአውሮፓ ውድድሮች በመታገዱ ደረጃው ከ11ኛ ወደ 16ኛ ዝቅ ማለቱን ዴሎይት አስታውቋል።
ከ1ኛ እስከ 20ና ደረጃን የያዙት አመታዊ ገቢ በ6 በመቶ ጨምሮ በድምሩ 9.47 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ስካይኒውስ ዘግቧል።