3 ዓመታት 15 “RB17 ሃይፐርካር” መኪናዎች ብቻ የሚመረቱ ሲሆን ሁሉም ከወዲሁ ተሸጠዋል
ሬድቡል “RB17 ሃይፐርካር” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የዓለማችን ውድ፣ ቅንጡና ፈጣን መኪና ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።
የፎርሙላ ዋን የመኪና ውድድር የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ሬድቡል ከ7.7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ የተቆረጠለት “RB17 ሃይፐርካር” መኪናውን ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው “ጉድውዱ የፍጠነት ፌስቲቫል” ላይ ይፋ ማድረጉም ተነግሯል።
አዲሱ የሬድቡል “RB17 ሃይፐርካር” መኪና በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።
“RB17 ሃይፐርካር” መኪና ውስን ምርት ብቻ ተመርቶ ለገበያ እንደሚቀርብ ያስታወቀው ሬድቡል፤ በቀጣይ 3 ዓመትት ውስጥ ለመደበኛ የመንገድ ላይ ጉዞ ብቻ የሚያገለግሉ 15 መኪናዎች ይመረታሉ ብሏል።
በቀጣይ 3 ዓመታት ውስጥ ለማምረት እቅድ የተያዘባቸው 15 “RB17 ሃይፐርካር” መኪናዎች ከወዲሁ እያንዳንዳቸው በ7.77 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተሸተው ማለቃቸውንም ነው ኩባንያው ያስታወቀው።
አዲሱ የሬድ ቡል መኪና ከ900 ኪሎ ግራም በታች ክብደት የሚኖረው ሲሆን፤ 1000 የፈረስ ጉብልት ያለው “V10 ኮስዎርዝ” ሞተር ከተጨማሪ ከ200 የፈረስጉልበት የኤልክትሪክ ሞተር የሚገጠምለት ነው ተበሏል።
በሁሉም “RB17 ሃይፐርካር” መኪና ላይ የሬድ ቡል የላቀ ቴክኖሎጂዎች በጠቅላላው የግንባታ ሂደት እንደሚተገበሩም ነው ኩባንያው ያስታወቀው።
በዓለማችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት በጣም ውድ የሆኑ ፈጣን እና ቅንጡ መኪናዎች ይፋ የሚደረጉ ሲሆን፤ የፈረንሳዩ ቡጋቲ በቅርቡ በሰዓት 445 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ መኪና መስራ ይታወሳል።
አዲሱ የቡጋቲ መኪና 1 ሺህ 800 የፈረስ ጉልበት ያለው ሲሆን በሰዓትም 445 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል በወቅቱ መገለጹ አይዘነጋም።
አዲሱ የቡጋቲ መኪና 4 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ የወጣለት ሲሆን የተወሰኑ የሙከራ ስራዎች ከተደረጉ በኋላ 250 ምርቶች ለገበያ ይቀርባሉ ተብሏል።
የቡጋ ተሽከርካሪ ሶስት የኤሌክትሪክ ሞተር እንዲሁም 1 ሺህ ፈረስ ጉልበት ያለው አንድ የነዳጅ ሞተርም እንዳለው ተገልጿል።