ቀይ ስጋ አብዝቶ መመገብ ለስኳር ህመም እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ገለጹ
ቀይ ስጋ አብዝቶ መመገብ የስኳር መጠናችንን ለማመጣጠን የሚረዳው ጣፊያ የተሰኘውን የሰውነት ክፍል ይጎዳል ተብሏል
በበርካቶች የሚወደደው ቀይ ስጋ ከስኳር ህመም ባለፈም እንደ አንጀት ካንሰር እና መሰል ተያያዥ ህመሞች እንደሚያጋልጥም ተገልጿል
ቀይ ስጋ አብዝቶ መመገብ ለስኳር ህመም እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያዊያን ተወዳጅ የሆነው ቀይ ስጋን አብዝቶ መመገብ ለስኳር ህመም እንደሚዳርግ የሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በአሜሪካ ስርዓተ ምግብ ጆርናል ላይ ይፋ የተደረገው ይህ የሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች ምርምር ውጤት ቀይ ስጋ አብዝቶ መመገብ ለአይነተ ሁለት የስኳር ህመም ይዳርጋል ተብሏል፡፡
ከቀይ ስጋ የሚገኘውን የምግብ ንጥረ ነገሮችንም እንደ ለውዝ ያሉ ምግቦችን በመመገብ መተካት እንደሚቻልም ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
ለስኳር ታማሚዎች ይጠቅማል የተባለው አዲሱ የአፕል ስማርት የእጅ ሰዓት
ተመራማሪዎቹ በምርምራቸው በሳምንት ሁለት ጊዜ ቀይ ስጋን መመገብ ለአይነተ ሁለት ስኳር ህመም የመጠቃት እድላችንን ያሰፈዋል ብለዋል፡፡
36 ዓመታትን ፈጅቷል በተባለው በዚህ ጥናት ላይ 200 ሺህ ቀይ ስጋ ተመጋቢዎች ተሳትፈዋል የጠባለ ሲሆን በ22 ሺህ ሰዎች ላይ ታይፕ 2 ስኳር በሽታ ተገኝቶባቸዋል ተብሏል፡፡
በተለይም የተቀነባበረ ቀይ ስጋ የሚመገቡ ሰዎች 46 በመቶ እንዲሁም ያልተቀነባበረ ቀይ ስጋ የሚመገቡ ሰዎች ደግሞ 24 በመቶ ለስኳር ህመም ተጋላጭ ናቸው እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
በቀይ ስጋ ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን ያለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ የምግብ መፈጨትን እና የሰውነታችንን የስኳር መጠን ለማመጣጠን የሚረዳው ጣፊያ የተሰኘውን የሰውነታችንን ክፍል ይጎዳል ተብሏል፡፡
ቀይ ስጋ መመገብ ከስኳር ህመም ባለፈ እንደ አንጀት ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ ህመሞች የመጠቃት እድላችንን እንደሚያሰፋውም ተገልጿል፡፡