በቀይ ባሕር ያለው የጸጥታ ችግር በኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ንግድ አንቅስቃሴ ላይ ችግር መፍጠሩ ተገለጸ
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ክፍተት እንዳይፈጠር የራሱን መርከቦች በማሰማራቱን አስታወቋል
የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር በተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ የመርከቦች እንቅስቃሴ ቀንሷል
በቀይ ባሕር የተከሰተውን የጸጥታ ችግር በኢትዮጵያ የገቢ እና የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ ችግር መፍጠሩን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ።
ለሃማስ አጋርነታቸውን የገለጹት የየመን ሃውቲ ታጣቂዎች እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ካላቆመች ከቴል አቪቭ ጋር ግንኙነት ባላቸው መርከቦች ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ መዛቱ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም የየመን ሃውቲ ታጣቂዎች በመርከቦች ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ሲሆን፤ በርካታ የመርከብ ድርጅቶች ቀይ ባህርን መጠቀም እንደሚያቆሙ መግለጻቸው አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ትናንት ባማበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ “በቀይ ባህር የተከሰተው የጸጥታ ችግር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና ከኢትዮጵያ የሚወጡ ጭነቶች ከጊዜና ከወጪ አንፃር የአገልግሎት ጥራት አግኝተው እንዳይገቡና እንዳይወጡ ችግር ሆኗል” ብሏል።
በወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ አብዛኛው ገቢ ጭነት ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ጋር ስምምነት ካላቸው ሌሎች አጓጓዥ መርከብ ድርጅቶች አማካኝነት ይጓጓዝ እንደነበረ ያስታወሰው ድርጅቱ፤ አሁን ግ ድርጅቶች ወደ ጅቡቲ መምጣት ማቆማቸውንም ጠቅሷል።
በዚህ ምክንያት አገልግሎት ክፍተት እንዳይፈጠር የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የኢትዮጵያ ገቢ ጭነቶች በብዛት ወደ ሚነሱባቸው ወደቦች የራሱን መርከቦች በማሰማራት እና ምልልሳቸውን በመጨመር ጭነቶች ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ከወጪ ንግድ ጋር በተያያዘም በተለይ የኢትዮጵያ ቡና ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚያጓጓዙ የመርከብ ድርጅቶች ወደ አካባቢው አለመምጣ ቡናን በተፈለገ ጊዜ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን ድርጅቱ ገልጿል።
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ የሚነሱ የወጪ ንግድ ጭነቶችን ወደ ቻይና ቲያንጂና ሻንጋይ፤ ወደ ህንድ ሙንድራና ናሃቫሼቫ እንዲሁም ወደ አረብ ኤምሬትስ ጀበል አሊና ሻርጃ ወደቦች በማጓጓዝ ላይ መሆኑንም አስታውቋል።
የየመኑ ሃውቲ ታጣቂ ጥቃትና ዛቻን ተከትሎ የአለማችን 10 በመቶ የንግድ መተላለፊያ የሆነውን ቀይ ባህር ውጥረት ውስጥ እንደከተተውም ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎም ግዙፍ የንግድ መርከብ ኩባንያዎች መርከቦቻውን ከቀቀይ ባር መስመር እያስወጡ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።
የዓለማችን ግዙፉ የንግድ ምርከብ ግሩፕ ሜትድትራኒያን ሸፒንክ ኩባንያ (ኤም.ኤስ.ሲ) እውጥር ተከትሎ መርከቦቹን ከቀይ ባህር አቅጣጫ ማስወጣቱን ካስታወቁት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው።
ሜርስክ በሚል መጠሪያው የሚታወቀው ግዙፉ የዴንማርክ የንግድ መርከብ ኩባንያም መርከቦቹን ከቀይ ባህር መስምር ማስወጣቱ ይታወሳል።
የጀርመኑ ሃፓግ ሎልዩድ የመርከብ ኩባንያም መርከቦቹን ወደ ቀይባህር እንደማይልክ ካስታወቀ ወራች ተቆጥረዋል።