በቀይ ባህር እየተካሄ ባለው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ሁለት መርከቦች መውጫ ማጣታቸው ተገለጸ
ተመድ እየበሰበሰች ካለችው መርከብ ላይ የተጫነውን በሚሊዮን በርሜል የሚቆጠረውን ነዳጅ ወደ አዲስ መርከብ ለማዛወር ጥረት አድርጎ ነበር
በምዕራባውያን የባህር ኃይል እና በየመን የሀውቲ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው የተኩስ ልውውጥ ምክያት ሁለት መርከቦች መውጫ አጥተዋል
በቀይ ባህር እየተካሄ ባለው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ሁለት መርከቦች መውጫ አጥተዋል።
በቀይ ባህር በምዕራባውያን የባህር ኃይል እና በየመን የሀውቲ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነዳጅ እና መርዛማ ቆሻሻ የጫኑ መርከቦች መውጫ አጥተው መቆማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከመርከቦቹ አንደኛዋ በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር በሚያልፉ መርከቦች ላይ ሚሳይል ከሚተኩሱበት እና ሀውቲዎች ኢላማ ያደረገ የአሜሪካ ሚሳይል ከሚያርፉበት ራስ ኢሳ ፖርት አቅራቢያ ለአመታት የቆመች ነች ተብሏል።
ባለፈው አመት ተመድ እየበሰበሰች ካለችው 'ኤፍኤስኦ ሴፈር' ከተሰኘችው መርከብ ላይ የተጫነውን በሚሊዮን በርሜል የሚቆጠረውን ነዳጅ 121 ሚሊዮን ዶላር ውጭ በማድረግ ወደ አዲስ መርከብ ለማዛወር ጥረት አድርጎ ነበር።
ተመድ በመርከቧ ላይ እስካሁን ተጭኖ ያለውን መርዛማ ውሃ ወደ ሌላ ቦታ ለመድፋት እና ነዳጁን ወደ ውጭ ለመሸጥ በማለም ነበር የተንቀሳቀሰው።
አለምአቀፍ እውቅና ያለው የሀውቲ መንግስት እና የሀውቲ ታጣቂዎች ከነዳጁ የሚገኘውን ገንዘብ ማን ይውሰድ በሚለው ጉዳይ ላይ ባለመስማማታቸው ምክንያት ሁለቱም መርከቦች ሊንቀሳቀሱ አልቻሉም።
የተመድ ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም(ዩኤንዲፒ) መርከቦቹን ለማንቀሳቀስ የመን ውስጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ እንደሚገኝ ገልጿል።
የዩኤንዲፒ ቃል አቀባይ የሀውቲ ታጣቂዎች መርከቦቹን ለማጥቃት ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳይ ምልክት የለም ሲሉ ተናግረዋል።
ነገርግን አለምአቀፍ እውቅና ያለው የየመን መንግስት እንዳለው ከሆነ የሀውቲ ታጣቂዎች መርከቦቹ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ጥለዋል።
በ1970ዎቹ የተሰራችው ግዙፏ 'ኤፍኤስኦ ሴፈር' መርከብ የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት በ2014 ከመፈንዳቱ በፊት ተንሳፋፊ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ሆና አገልግላለች።