በአሜሪካ ይፋ የተደረገው የቀይ ባህር ትራንስፖርት ጥበቃ ቡድንን የተቀላቀሉ ሀገራት እነማን ናቸው?
የየመን አማጺዎች ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን መርከቦች መምታቱን ተከትሎ የቀይ ባህር ትራንስፖርት ችግር ውስጥ ወድቋል
ኔቶን ጨምሮ 39 ሀገራት አባል የሆኑበት የባህርሀይል ጥምረት የተሰኘ ሀይል አስቀድሞ ቀይ ባህርን ለመጠበቅ የተቋቋመ ቢሆንም የሁቲ ታጣቂዎች ጥቃት ማድረስ ችለዋል
በአሜሪካ ይፋ የተደረገው የቀይ ባህር ትራንስፖርት ጥበቃ ቡድን የተቀላቀሉ ሀገራት እነማን ናቸው?
ለፍልስጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ ከ75 ቀናት በፊት በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ጦርነት መቀስቀሱ ይታወሳል።
እስራኤል በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ከ20 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ሲገደሉ ከ1ሺህ 200 በላይ እስራኤላውያንም ተገድለዋል።
የእስራኤልን የጋዛ ጥቃት ተከትሎ በርካታ ሀገራት እና ተቋማት ያወገዙ ሲሆን የየመኑ ሁቲ ታጣቂ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው መርከቦች ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ነው።
የሁቲን ጥቃት ተከትሎ የቀይ ባህር ትራንስፖርት አደጋ ላይ የወደቀ ሲሆን ይህን የዓለም ንግድ መሳለጫ መስመር ከአደጋ ለመጠበቅ በአሜሪካ የሚመራ የባህር ሀይል ጥበቃ ቡድን ይሰማራል ተብሏል።
በአሜሪካንይፋንየተደረገውን ይህን ሀይል በርካታ ሀገራት እንደሚቀላቀሉ የገለጹ ሲሆን ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ግሪክ፣ ኔዘርላንድ እና ስፔን ዋነኞቹ ናቸው።
ይህን የንግድ መስመር ከባህር መርከብ አጋቾች ለመጠበቅ በሚል ኔቶ እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ 39 ሀገራት አስቀድመው በአካባቢው ባህር ሀይላቸው ያሰማሩ ቢሆንም የሁቲ አማጺያን ግን ጥቃት ማድረስ እንደቻሉ ሮይተርስ ዘግቧል።
አማጺያኑ እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን ጥቃት ካላቆመች በቀይ ባህር ላይ ጥቃት ማድረሱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።