"ሬድበርድ አይኤምአይ" አለምአቀፉን የሚዲያ ኩባንያ "ኦል3 ሚዲያ"ን መግዛቱን አስታወቀ
"ሬድበርድ አይኤምአይ" ፣ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ኢንቨስትመንትንስ (አይኤምአይ) እና ሬድበርድ ካፒታል ፓርትነርስ በጋራ የመሰረቱት የጋራ ኢንቨስትመንት ወይም ጆይንት ቬንቸር ነው
የኦል3 ኩባንያዎች በመላው አለም በነጻ እና በክፍያ በቴሌቭዥን የሚተላለፉ 4000 ሰአት የሚረዝም ይዘት በየአመቱ የማዘጋት አቅም አላቸው
"ሬድበርድ አይኤምአይ" አለምአቀፉን የሚዲያ ኩባንያ "ኦል3 ሚዲያ"ን መግዛቱን አስታወቀ።
"ሬድበርድ አይኤምአይ" በአሜሪካ፣ በዩናይትድ ኪንግደም እና በጀመርን አስፈላጊውን የህግ ሂደት ካጸደቀ በኋላ በታሪኩ ትልቅ የተባለውን ግዥ ማጠናቀቁን አስታውቋል።
በመላው አለም በሚዲያ፣ በመዝናኛ፣ በስፖርት እና በዜና ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ሬድበርድ አይኤምአይ በዓለም ትልቅ ከሚባሉት አንዱ የሆነውን የቴሌቪዥን እና የፊልም ፕሮዳክሽን ኩባንያ "ኦል3 ሚዲያ"ን ከሶስት ባለቤቶቹ ገዝቷሎ።
ሶስቱ ባለቤቶች ብሮስ. ዲስከቨሪ ኢንክ.(ናስዳቅ:ደብሊውቢዲ) እና 'ላይቤሪቲ ግሎባል ሊሚትድ' ፣ (ናስዳቅ እንዴክስ: ኤልቢቲዋይኤ, አልቢቲዋይኬ) ናቸው። ሬድበርድአይኤምአይ ግዥውን ለመፈጸም 1.5 ቢሊዮን ፓውንድ ወስዶበታል።
የሬድበርድ አይኤምአይ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀፍ ዙከር፣ የኦል3 ሚዲያ ሊቀመንበር ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የአሁኑ ስራ አስፈጻሚ ጄን ቱርቶን እና ቺፍ ኦፐሬሽን ኦፊሰራ ሳራህ ጌተር ኦል3 ሚዲያን መምራታቸውን እንደሚሸጥሉ ያሆ ፋይናንስ ዘግቧል።
"ሬድበርድ አይኤምአይ" ፣ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ኢንቨስትመንትንስ (አይኤምአይ) እና ሬድበርድ ካፒታል ፓርትነርስ በጋራ የመሰረቱት የጋራ ኢንቨስትመንት ወይም ጆይንት ቬንቸር ነው።
በዚሁ መሰረት የአይኤምአይ ዋና ስራ አስፈጻሚ ራኒ ራአድ የኦል3 ሚዲያ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነዋል።
መቀመጫውን አቡዳቢ ያደረገው አይኤምአይ የግል የሚዲያ ኢንቨስትመንት ኩባንያ ሲሆን በስሩም በመካከለኛው ምስራቅ፣ በሰሜን አፍሪካ እና ከእዚያ ባሻገር ጠንካራ ተደራሽነት ያላቸው ታዋቂ የሚዲያ ብራንዶችን ወይም ስሞች ባለቤትነት ነው።
የአይኤምአይ "ዘ ናሽናል"፣ "ሲኤንኤን አረቢክ እና "አል ዐይን ኒውስ"ን የተባሉ ታዋቂ የሚዲያ ብራንዶችን የሚያካትት ሲሆን በ"ዩሮ ኒውስ"ም የተወሰነ ድርሻ ያለው ነው።
መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ኦል3 ሚዲያ በእንግሊዝ በጣም ግዙፉ የፕሮዳክሽን ኩባንያ ሲሆን በስሩም "ስቱዲዮ ላምበርት"፣ "ሮው"፣ "ቱ ብራዘርስ ፒክቸርስ" ፣ "ሲልቨርባክ ፊልምስ"፣ "ኒው ፒክቸርስ" እና በአለም ምርጥ የሚባሉ ፕሮግራሞችን የሚያዘጋጀውን "ኔይል ስትራት ፕሮደክሽን"ን ጨምሮ በኦዲዮቪዡዋል ስራ የተሰማሩ ከ50 በላይ ብራንጆች አሉት።
የኦል3 ኩባንያዎች በመላው አለም ከፍ ያለ ተደራሽነት ያላቸው ሲሆን በነጻ እና በክፍያ በቴሌቭዥን የሚተላለፉ 4000 ሰአት የሚረዝም ይዘት በየአመቱ የማዘጋት አቅም አላቸው።