ፖለቲካ
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሸሙ
ትዕግስ ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬ ሹመቶችን ሰጥተዋል
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማው ተገለጸ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን መስጠታቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በዚህም መሰረት አምባሳደር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው ተገልጿል።
አምባሳደር ሬድዋን በዛሬው እለት ምክክት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሸሜትን አቶ ተመስገን ጥሩነህን በመተካት ነው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሸሙት።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር በመሆንም በማገልገል ላይ እንደነበሩ ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የሰጡት ሌላኛው ሹመት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዳይሬከተር ሲሆን፤ በዚህም ትዕግስ ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
ትዕግስ ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዳይሬከተር የነበሩትን አቶ ሰለሞን ሶካን የሚተኩ ይሆናል።