አንጋፋው ሴኔጋላዊ የሙዚቃ አቀንቃኝ ቲዮን ሴክ በ66 ዓመቱ አረፈ
ቲዮን ሴክ ከሚታወቅባቸው ምቶች መካከል “አልሎ ፔቲት” እና “ኦሬንተሲም"ን ይገኙበታል
ሴክ “አንዱ የኛ ዘመን ጀግና ነው”-የቀድሞ ጋዜጠኛና የአሁኑ የፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አማካሪው ሀጂ ሀሚዶ ካሴ
ላለፉት አራት አስርት አመታት በሰኔጋል ገነው ከወጡ የሙዚቃ ኮኮቦች፤ አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ቲዮን ሴክ በትላትናው እለት ህይወቱ እንዳለፈ ጠበቃው ተናግረዋል፡፡ "ባደረበት ህመም ምክንያት ዛሬ በዚህ በፋን ሆስፒታል አርፈዋል" ሲሉም ለኤ.ኤፍ.ፒ ተናግረዋል ጠበቃው ኦስማኔ ሰየ፡፡
ከ “ግሪዮት” የዘፋኞች ቤተሰብ ተገኘው ቲዮን ባላጎ ሴክ፤ ከሀገሩ አለፎ በምእራብ አፍሪካ ተዋዳጅ ከሆኑ እንደነ ዩዋሱ ንዶር፤ኦማር ፔን፤ኢስመዒል ሎ እንዲሁም ልጁ ዋሊ ሴክ የመሳሰሉ ዝነኛ ሙዚቀኞች ተርታ ሊጠቀስ የሚችል እንደነበርም ነው በርካቶች በመናገር ላይ ያሉተ፡፡
በ 1970 ዎቹ በአፍሮ-ኩባ - ሳልሳ እና በባህላዊው የሴኔጋል ሙዚቃ ድብልቅ በመጫወት በሚታወቀው ኦርቸስተር ባባብ ውስጥ ውስጥ ዝፈነዋል፡፡
የዜማና እና የግጥም ጥምር ባለሙያው ቲዮን ባላጎ ሴክ፤ ራማ ዳምን በ 1980 ውስጥ የመሰረተ ሲሆን ይህም ‹ፈንባክ› ፣ ሬጌን ፣ የዳንስ ሙዚቃን እና የአከባቢን ቅኝቶችን የሚያጣምር ዘውግ ከሚባል የባህላዊ ማጽጃዎች መካከል አንዱ ሆኗል ፡፡
ከሚታወቅባቸው ምቶች መካከል ‹አልሎ ፔቲት› ፣ ‹ ኦሬንተሲም › እና ‹ዲያጋ› ን ይገኙበታል ፡፡
የዝነናኛው እረቲስት ህልፍት ተከትሎም ታድያ በርካቶች ሀዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ የቀድሞው የዳካር ካሊፋ ሳል ከንቲባ “ለእውነተኛው የሴኔጋል ሙዚቃ ሀውልት” ምስጋና ይገበዋል ማለታቸው ተዘግበዋል፡፡
ሴክ “ አንዱ የኛ ዘመን ጀግና ነው” በማለት በትዊትር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩት ደግሞ ደግሞ የቀድሞ ጋዜጠኛና የአሁኑ የፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አማካሪው ሀጂ ሀሚዶ ካሴ ናቸው፡፡
የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት፤ ሴክ እሁድ ከሰዓት በኋላ በዮፍ ዳካር አካባቢ በሚገኘው የመቃብር ስፍራ የቀብር ስነ ስርዓቱ ተፈጽመዋል፡፡ ፡፡
የዘፋኙ የመጨረሻ ዓመታት በተለይም በ2015 50 ሚልዮን የሚገመት ሐሰተኛ ገንዘብ ተገኝቶበታል በሚል ቅሌት ለ ዘተን ወራት ያክል ታስሮ የተፈታበትና ስሙ በጥሩ ሁኔታ የማይነሳበት ከባድ ጊዝያት እንደነበሩ የሚታወስ ነው፡፡