ልዩልዩ
ፈጣን የደም ምርመራ በማካሄድ አንድ ሰው በኮሮና መያዙንና አለመያዙን ማወቅ እንደሚቻል ተማራማሪዎች ገለፁ
አንድ ሰው አውሮፕላን ውስጥ ለመግባት በሚጠባበቅበት ጊዜ ምርመራውን በቀላሉ ሊያደረገው ይችላል
የምርመራው ውጤት ከ5 ደቂቃዎች ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ተገልጿል
የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ቡድን በደቂቃዎች ውስጥ ፈጣን የደም ምርመራን በማካሄድ አንድ ሰው የኮሮና ክትባት መውሰድ አለመውሰዱን መለየት እንደሚቻል አስታወቀ፡፡
ተማራማሪዎቹ አንድ ሰው የኮሮና ክትባት መከተቡን ወይም አለመከተቡን የሚያሳይ ፈጣን የደም ምርመራም አካሂደዋል፡፡
ምርመራው አንድ ሰው አውሮፕላን ውስጥ ለመግባት ወይም ወደ አንድ የስፖርት ቦታ ለመግባት በሚጠባበቅበት ጊዜ በቀላሉ ሊያደርገው የሚችለው እንደሆነም ነው ተማራማሪዎቹ የገለጹት፡፡
ፈጣኑ የደም ምርመራ የሰው ልጆች ወደ መደበኛ ህይወታቸው ለመመለስ እያደረጉት ባለው ጥረት፣ ማን እንደተከተበና እንዳልተከተበ በማወቅ ራሳቸውን ከኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያስችል ነውም ተብሎለታል፡፡
ለኮቪድ -19 የሚደረገው ምርመራ አንድ ሰው የደም አይነቱን ለመለየት በቤት ውስጥ ከሚያደርገው ምርመራ ጋር ተመሳሳይ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡
ከተጠቃሚው ጣት ደም በመውሰድ ከ5 ደቂቃዎች ባነሰ ጊዜ ውስጥ ውጤቱን ይፋ ለማድረግ የሚያስችል የደም ምርመራ እንደሆነም ተማራማሪወቹ አስታውቀዋል፡፡