በምድር ከ73ሺ በላይ የዛፍ ዝርያዎች እንዳሉ በዘርፉ ጥናት ያካሄደ የተመራማሪዎች ቡዱን አስታወቀ
ጥናቱ የተካሄደው በ90 ሀገራት ውስጥ ነው ተብሏል

ደቡብ አሜሪካ፣አፍሪካ እና ኤስያ በርካታ የዛፍ ዝርያዎች ካሉባቸው ክፍለ-ዓለማት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው
በምድራችን ከ73 ሺ ባለይ የዛፍ ዝርያዎች እንዳሉ በዘርፉ ጥናት ያደረገ የተመራማሪዎች ቡዱን አስታወቀ፡፡
140 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች ያቀፈው ቡዱን ባደረገው ጥናት እንዳመላከተው ከሆነ፤ በዓለማችን 73 ሺ 300 የዛፍ ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህም 9ሺ 200 የሚሆኑት ገና ጥናት የሚደረግባቸው ናቸው፡፡
ይሁን አንጅ በቀጣይ ጥናት ከሚደረግባቸው የዛፍ ዝርያዎች በተለይም በሞቃታማ አከባቢዎች የሚገኙ ዛፎች (tropical trees) ከአየር ለውጥ ጋር በተየያዘ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ጥናቱን ያካሄዱት የዘርፉ ተመራማሪወች ገልጸዋል፡፡
ወደዚህ መደምደምያ ለመድረስ በሚልዮኖች በሚቆጠሩ ዛፎች ላይ ምርመር መካሄዱን ያስታወቀው የተመራማሪ ቡዱኑ ጥናት፤ በቀጣይ የመጥፈት አደጋ የተጋረባቸውን ዝርያዎች ለመታደግ በርካታ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡
ጥናቱ የተካሄደው በ90 ሀገራት በሚገኙ 38 ሚልዮን ዛፎች ላይ መሆኑም ነው የተመራማሪዎች ቡዱኑ ያስታወቀው፡፡
ዛፎቹ ለምግብ፣ መድሃኒት እንዲሁም የካርቦን ዳይኢክሳይድ መጠን ትልቅ አስተዋጽኦ አንዳለቸውም ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
በሚኒሶታ ዩኒቭረሲቲ ተመራማሪና የቡዱኑ መሪ ዶክተር ፔተር ሪች ፤ የተካሄደው ጥናት " የሚበዛው የዛፎች ዝርያ በየት አከባቢ በብዛት እንደሚገኝ እንድንረዳ አስችሎናል" ብለዋል፡፡
ደቡብ አሜሪካ፣አፍሪካ፣ኤስያ እና ኦሺንያ የተመራማሪዎቹ ቀጣይ መዳረሻዎች ሊሆኑ እንደሚችሉም ጠቁሟል ዶክተር ፔተር ሪች፡፡
በደቡብ አሜሪካ 43 በመቶ፣ በውሮፓና ኤስያ (ዩሮሽያ) 22 በመቶ፣ በአፍሪካ 16 በመቶ፣ በሰሜን አሜሪካ 15 በመቶ እንዲሁም በኦሺንያ 11 በመቶ የዛፍ ዝርያዎች እንደሚገኙም የተመራማሪዎቹ ቡዱን መሪው ዶክተር ፔተር ሪች ተናግረዋል፡፡