ሩሲያ በወታደራዊ ዝግጅቷ ለቁስለኞች የሚሆን ደም ማካተቷን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናገሩ
የሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የሩሲያ ወረራ የማይቀር ነው ሲሉ ተንብየዋል
ሩሲያ የኔቶ አባል በሀገራት ከቀድሞው የሶቨት ህብረት ሀገራት እንዲርቁ ማስጠንቀቋ ይታወሳል
ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በምታደርገው ዝግድት ለቁስለኞች የሚሆን ደም ጭምር ያከተተ መሆኑን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናገሩ
የአሜሪካ ባለስልጣናት አይቀሬ ነው ባሉት የሩሲያ ወታደራዊ ዝግጅት፣ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ የምታደርገው ወታደራዊ ዝግጅት ቁስለኞችን ለማከም ደምና ሌሎች የመድሃት አቅርቦቶችን እንደሚጨምር የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የቀድሞ እና የአሁን የአሜሪካ ባለስልጣናት የደም አቅርቦት፣ ፕሬዝዳንት ፑቲን ከወሰኑ፤ ሩሲያ ዩክሬንን ልትወር እንደምትችል ወሳኝ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
አሜሪካ፤ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ከ100ሺ ባለይ ወታደሮችን ማስጠጋቱን እና ወረራም ልትፈጽም እንደምትችል ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡
የሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የሩሲያ ወረራ የማይቀር ነው ሲሉ ተንብየዋል፤የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ደግሞ ሩሲያ በአጭር ጊዜ ዩክሬንን ልትወር ትችላለች ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ ከሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር መረጃ ማግኘት አለመቻሉን ገልጿል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ዙሪያ ያለው የኔቶ ሃይል መሰባሰብ እንዳሳሰባትን እንዲቆም በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡ ዩክሬን የኔቶ ጦር አባል መሆን የለባትም፤የኔቶ አባል በሀገራትም ከቀድሞው የሶቨት ህብረት ሀገራት እንዲርቁ ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡