ፖሊስ ጣልቃ በመግባት የውሃ መድፍ በመዘርጋትና አስለቃሽ ጭስ መጠቀም ለማረጋጋት ሞክሯል
በኳታር የዓለም ዋንጫ ቤልጅየም በሞሮኮ መሸነፏን ተከትሎ በብራስልስ ሁከት ተስቷል።
በትናትናው እለት በበኳታር የዓለም ዋጫ በምድብ 6 የተደለደሉት ቤልጂየም እና ሞሮኮ ያደረጉት ጨዋታ በሞሮኮ 2ለ0 አሸናፊነት መጠነቀቁ ይታወሳል።
የህንን ተከትሎም በውጤቱ የተናደዱ ቤልጄማውያን ንዴታቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውም ታውቋል።
ሁከቱን ተከትሎም የወደብ ከተማ በሆነችው ሮተርዳም ሁለት የፖሊስ ባለስልጣናት መቁሰላቸውንም ተነግሯል።
ሁከቱን ተከትሎም የቤልጂየም ፖሊስ በሮተርዳም ከተማ 12 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።
በብራሰልስ እና በሰሜናዊቷ አንትወርፕ ከተማ ስምንት ተጨማሪ ሰዎችን ለመበተን የውሃ መድፍ እና አስለቃሽ ጭስ ካሰማራ በኋላ ፖሊስ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን አስሯል።
ሁከቱ የተካሄደው በቤልጂየም ዋና ከተማ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ሲሆን የተወሰኑት የሞሮኮ ባንዲራ የለበሱ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።
የፖሊስ ቃል አቀባይ ኢልሴ ቫን ደ ኪሬ ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ አካባቢው መረጋጋቱን ጠቅሰው በሚመለከታቸው ስፍራዎች የመከላከያ ጥበቃዎች እንዳሉ ይቆያሉ ብለዋል።
"ሁከት ፈጣሪዎቹ ቁሳቁሶችን፤ ዱላዎችን ተጠቅመው በሕዝብ አውራ ጎዳን አቃጥለዋል" ሲል ፖሊስ ተናግሯል።
"በተጨማሪም አንድ ጋዜጠኛ በፈነዳ ርችት ፊቱ ቆስሏል። በእነዚህ ምክንያቶች ነው በፖሊስ ጣልቃ ገብነት የውሃ መድፍ በመዘርጋት እና አስለቃሽ ጭስ መጠቀም እንዲቀጥል የተወሰነው" ሲል ፖሊስ መናገሩን ሮይተርስ ዘግቧል።