በራሪው ሞተር ሳይክል በቀጣዩ 2023 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል
የጃፓኑ ዚቱሪስሞ ኩባንያ የዓለማችን የመጀመሪያው በራሪ ሞተር ሳይክል ከሰሞበኑ ይፋ አድርጓል።
በአሜሪካ ዴትሮይት እየተካሄደ ያለው አውቶሞቲቭ ሾው ላይ የቀረበው በራሪው ሞተር ሳይክል የበርካቶችን ቀልብ ይዟል።
በራሪ ሞተር ሳይክሉን የጃፓኑ ዚቱሪስሞ ኩባንያ የሰራው ሲሆን፤ ሞተር ሳይክሉ ለ40 ደቂቃ ያክል አየር ላይ መብረር ይችላል።
ዚቱሪስሞ በራሪ ሞተር ሳይክሉ በሰዓት እስከ 100 ኪሎ ሜትር ፍጥነት መብረር የሚችል መሆኑንም ኩባንያው አስታውቋል።
የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ ሹሄሂ ኮማስቱ፤ ኩባንያው ከበራሪ ሞተር ሳይክል በተጨማሪ ድሮኖች እና በራሪ መኪናዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አዲሱ በራሪ ሞተር ሳይክል አሁን ላይ በጃፓን መሸጥ ጀምሯል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፤ በአሜሪካ እና በሌሎች የዓለም ሀገራት ከ2023 ጀምሮ ለገበያ ይቀርባል ብለዋል።
አዲሱ በራሪ ሞተር ሳይክል አሁን ላይ የተገመተለት ዋጋም 777 ሸህ ዶላር ነው።
የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ ሹሄሂ ኮማስቱ፤ እስከ ፈረንጆቹ 2025 ባለው ጊዜ በኤሌክትሪ የሚሰራውን በራሪ ሞተር ሳይክል ዋጋ ወደ 55 ሺህ ዶላር የመቀነስ ተስፋ እንዳለ አስታውቀዋል።