ከሜሴ ጋር እሰጣገባ ውስጥ ገብቶ የነበረው ብራዚላዊ አጥቂ በማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቹ ዘረኝነትን የሚያንጸባርቁ መልእክቶች እንደደረሱት ተናግሯል
ብራዚላዊው አጥቂ ሮድሪጎ የዘረኝነት ስድብ እንደደረሠሰበት ገለጸ።
ባለፈው ማክሰኞ አርጀንቲና እና ብራዚል የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከማድረጋቸው በፊት ከሜሲ ጋር እሰጣገባ ውስጥ ገብቶ የነበረው ብራዚላዊ አጥቂ ሮድሪጎ በማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቹ ዘረኝነትን የሚያንጸባርቁ መልእክቶች እንደደረሱት ተናግሯል።
አርጀንቲና ብራዚልን 1-0 ያሸነፈችበት በብራዚል ሪዮ ዲ ጀነሪዮ ማራካና ስቴድየም የተካሄደው ጨዋታ፣ የብራዚል ፖሊስ ከአርጀንቲና ደጋፊዎች ጋር በመጋጨቱ ምክንያት ከተያዘለት መርሃግብር 30 ደቂቃ ዘግይቶ ነበር የተጀመረው።
ፖሊሶችን በጭካኔ የከሰሰው ሜሲ፣ ከብራዚሉ ካፓቴን ማርኩኒሆስ እና የዘረኝነት መልእክቶች እንደደረሱት ከገለጸው ሮድሪጎ ጋር ጠንካራ ቃላትን ሲቀያየር ታይቷል።
ሮዲራጎ ዘረኝነትን የሚገለጹ የዝንጀሮ እና የሙዝ 'ኢሞጂዎች' ደርሰውኛል ብሏል።
ሮድሪጎ በኢንስታግራም ገጹ ላይ "ዘረኞች ሁሌም ስራ ላይ ናቸው። ማህበራዊ ሚዲያዎች በስድብ እና በማይረቡ ነገሮች ተጥለቅልቀዋል" ብሏል።
"እንደሚፈልጉት ካልሆንላቸው፣ እንደሚፈልጉት ካልተንቀሳቀስን እና የኛ ብቻ ነው ብለው የሚያስቡትን ቦታ የያዝን ሲመስላቸው" ወንጀለኛ ባህሪያቸው ይገለጣል ሲል ሮድሪጎ ጽፏል።
ሮድሪጎ ስድብ ቢሰነዘርበትም ስራውን እንደማያቆም ተናግሯል።
በተደጋጋሚ የዘረኝነት ስድብ ሰለባ የሆነው ቪንሺየስ ጁኒየርም ለሮድሪጎ አጋርነቱን አሳይቷል።
ቪንሺየስም "አናቆምም" ሲል በማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቹ ጹፏል።
ቪንሺየስ እና ኔይማር ያልተሳተፉበት የብራዚል ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው በአርጀንቲና ሽንፈትን አስተናግዷል።