ሁለት ሀገራት የአውሮፓ ህብረቱን ድንበር አልባ ሸንገን ዞን ሙሉ በሙሉ ተቀላቀሉ
ሁለቱ ሀገራት ያለፖስፖርት ቁጥጥር የሚንቀሳቀሱ ዜጎች ያሏቸውን የሀገራት ቡድን ተቀላቅለዋል
በፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ቤልጄየም፣ ኔዘርላንድስ እና ለክሰንበርግ መካከል የድንበር ቁጥጥር የቀረው በ1985 ነበር
ሁለት ሀገራት የአውሮፓ ህብረቱን ድንበር አልባ ሸንገን ዞን ሙሉ በሙሉ ተቀላቀሉ።
ሮማኒያ እና ቡልጋሪያ የድንበር ቁጥጥራቸውን በማንሳት ነጻ ዝውውር የሚካሄድበትን የአውሮፓ ህብረት ሸንገን ዞንን ሙሉ በሙሉ በዛሬው እለት መቀላቀላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሁለቱ ሀገራት ያለፖስፖርት ቁጥጥር የሚንቀሳቀሱ ዜጎች ያሏቸውን የሀገራት ቡድን ተቀላቅለዋል።
ትናንት ምሽት የቡልጋሪያ እና ሮማኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዳኑቤ ወንዝ ላይ የነበረውን ኬላ ካነሱ በኋላ ሩሴ በተባለችው የቡልጋሪያ የድንበር ከተማ ርችቶች ወደ ሰማይ ተተኩሰዋል። ማቋረጫው ለአለምአቀፍ ንግድ ወሳኝ መተላለፊያ ነው።
በቡልጋሪያ እና ሮማኒያ መካከል በሚደረገው የአየር እና የባህር ጉዞ ላይ ሲደረግ የነበረው ቁጥጥር ባለፈው ሚያዝያ ወር የተነሳ ቢሆንም የመሬት ጉዞ ግን ኦስትሪያ ህገወጥ ስደትን ለመከላከል በቂ ስራ አልተሰራም በሚል ውድቅ እስካደረገችበት ድረስ ቀጥሎ ነበር።
በፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ቤልጄየም፣ ኔዘርላንድስ እና ለክሰንበርግ መካከል የድንበር ቁጥጥር የቀረው በ1985 ነበር። የሸንገን ዞን በአሁኑ ወቅት 27 አባላት ካሉት የአውሮፓ ህብረት ውስጥ 25ቱን እንዲሁም አይስላንድን፣ ሊቸንስቲንን፣ኖርዌንን እና ስዊዘርላንድን ይሸፍናል።
አየርላንድ እና ሲፕረስ የሸንገን ዞን አባል አልሆኑም።