ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን በርካታ ጊዜ የተሰለፈ ተጫዋች በመሆን ክብረወሰን ሰበረ
ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል
ሮናልዶ በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠራውን ግቦች ብዛትም 120 ማድረስ ችሏል
ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንደፈረንጆቹ በ2003 አንጋፋውን የእንግሊዝ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋለ በዓለም እግር ኳስ መድረክ ነግሶ ለበርካታ ዓመታት መዝለቅ የቻለ ድንቅ ተጫዋች መሆኑ ይታወቃል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ታሪኩ በርካታ ክብረወሰኖችን በእጁ በማስገባት የሚታወቅ ሲሆን፤ ትናንት ምሽትም አዲስ ክብረወሰን መስበሩን ቢቢሲ አስነብቧል።
በዚህም የ38 ዓመቱ ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትናንት ምሽት በተሰለፈበት እና ሀገሩ ፖርቹጋል ሌችተንስታይንን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ በመሰልፍ ሁለት ጎሎችን በቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በጨዋታው መሰለፉን ተከትሎ ሮናልዶ ለሀገሩ 197 ጨዋታዎችን በማድረግ ለብሔራዊ ቡድን በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ በኩዌቱ አጥቂ ባድር አል ሙታዋ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በእጁ ማስገባት ችሏል።
በተጨማሪም የ38 ዓመቱ ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠራውን ግቦች ብዛትም 120 ማድረስ ችሏል።
ለሳዑዲው አልናስር የሚጫወተው ሮናልዶ በቀድመው የፖርቹጋል አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ የቋሚ አሰላለፍ እድል ተነፍጎት የነበረ ሲሆን በአዲሱ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ደግሞ የቡድኑ አምበል እና ቋሚ ተሰላፊ መሆን ችሏል።
ሀገሩ ፖርቹጋልን በመወከል ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 2003 የመጀመሪያ ጨዋታዉን ያደረገው ክርስቲያ ሮናልዶ፤ በ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ በመሳተፉ፤ 5 የዓለም ዋንጫዎች ላይ መሰለፍ የቻለ የዓለማችን ብቸኛው የእግር ኳስ ተጫዋች መሆንችሏል።
ክርስቲያኖ ሮናላዶ በእከ,ግር ኳስ ህይወቱ ያስመዘገባቸው ክብረወሰኖች
• በቻምፒየነስ ሊግ ላይ በርካታ ግቦችን ያስቆጠረ (140 ጎሎች)
• በቻምፒየንስ ሊግ ላይ በርካታ ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ (183 ጨዋታዎች)
• በቻምፒየነስ ሊግ በርካታ ጊዜ ዋጫ ያነሳ (5 ዋንጫዎች)
• በቻምጲየንስ ሊግ በርካታ የፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ የተሳተፈ (በ5 የፍጻሜ ጨዋታዎች)
• በቻምፒየንስ ሊግ ፍጻም ላይ ጎሎችን ያስቆጠረ (በ3 የፍጻ ጨዋታዎች)
• በቻምፒየንስ ሊግ ፍጻም ላይ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረ (14 ጎሎች)
• በዓለም እግር ኳስ በርካታ ኢንተርናሽናል ጎሎችን ያስቆጠረ (120 ጎሎች)
• በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በርካታ ሀትሪኮችን የሰራ የመጀመሪያው ተጫዋች (10 ሀትሪክ)