ሮናልዶ አድናቂው ከሆነውና በዩቲዩብ ታዋቂነትን ካተረፈው ኳታራዊ ጋር ተገናኘ
ፖርቹጋላዊው ኮከብ የዓለም ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ አል-ናስርን የተቀላቀለው ከቀናት በፊት ነበር
ኳታራዊዉ ጋኒም አል-ሙፍታህ በዓለም ዋንጫው ከሞርጋን ፍሪማን ጋር በፈጠረው ጥምረት የመድረኩ ፈርጥ እንደነበር ይታወሳል
በእግር ኳስ ታሪክ የዓለም ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ የሳኡዲ አረቢያውነሰ ክለብ አል-ናስር የተቀላቀለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ክለቡ አል ናስር አል ታይን 2-0 በረታበት ጨዋታ ባይሰለፍም በሜዳ ተገኝቶ ጨዋታውን መመልከቱ አይዘነጋም፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያልተሰለፈበት ዋና ምክንያት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቆይታው የቀድሞ ክለቡ ማንቸስተር ከኤቨርተን ጋር ባደረገው የኤፍ.ኤ 2021/2022 የውድድር ዘመን ላይ ጨዋታ ባሳየው ተገቢ ያልሆነ ባህሪ ምክንያት በእንግሊዝ ኤፍኤ የተጣለበትን ሁለት የጨዋታ እገዳ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
ከጨዋታው በኋላ የ37 አመቱ ፓርቹጋላዊ ኮከብ ሁለት ደጋፊዎችን አግኝቶ ፎቶግራፎችን ሲሰነሳ ታይቷል፡፡
ከአድናቂዎች አንዱ በዩቲዩብ ታዋቂነትን ያተረፈውና የዓለም ዋንጫ ድምቀት የነበረው ኳታራዊው ጋኒም አል-ሙፍታህ አንዱ ነው፡፡
የኳታር ዜጋ የሆነው ጋኒም አል-ሙፍታህ ካዱዋል ሪግረሽን ሲንድሮም(ሲዲኤስ) በተባለ ችግር ምክንያት ከወገብ በታች አካል እንደሌላው ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጅ የ20 ዓመት ወጣቱ ጋኒም አል-ሙፍታህ በዓለም ዋንጫው ከአሜሪካዊው ፊልም ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማን ጋር በፈጠረው ጥምረት የመድረኩ ፈርጥ መሆን የቻለ ነበር፡፡
ይህ ወጣት ታዲያ የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ አድናቂ ነው ይለናል ኦፔራ ኒውስ በዘገባው፡፡
በዚህም የሮናልዶ እና የጋኒም አል-ሙፍታህ መገናኘት የበርካቶች ቀልብ የሳበበ ጉዳይ መሆኑ በርካቶች በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡
የፖርቹጋላዊው አጥቂ ወደ ሳኡዲ ፕሮፌሽናል ሊግ መምጣት ሳዲን ጨምሮ በዓረቡ ዓለም የእግር ኳስ አብዮት ሊፈጥር የሚችል ትልቅ እድል እንደሆነ ይነሳል፡፡
የአል ናስር ክለብ አሰልጣኝ ፈረንሳዊው ሩዲ ጋርሽያ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ እንደ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የመሰሉ የተሟላ ክህሎት ያላቸው ተጨዋቾች በሳኡዲ ፕሮ ሊግ መመልከት " የሚደንቅ ነው " ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
ወደ ሳኡዲ ከማቅናቱ በፊት የተለያዩ ክለቦች ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ቢሆንም የሳኡዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ምርጫ ማድረጉ የገለጸው ሮናልዶ በበኩሉ ፤ “ለአል-ናስር መፈረሜ በህይወቴ የምኮራበት ውሳኔ ነው” ሲል ተናግሯል፡፡