የሳዑዲ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሮናልዶን ስለ ጉዳዩ እንዲያብራራም ጠርቶታል
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሳዑዲ ሊግ ጨዋታ ላይ ባሳየው ያልተገባ ባህሪና የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎችን በምልክት በመዝለፍ ሶስት ቀጣቶች እንደተላለፉነት ተሰምቷል።
የሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ አል ናስር ከአልሸባብ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ክርስቲያኖ ሮናዶ ያደረገውን አሳፋሪ ተግር አስመልክቶ ውሳኔውን አሳልፏል።
የሮናልዶ ቡድን አልናስር አልሻባብን 3 ለ 2 ባሸነፉበት ጨዋታ ማጠናቀቂያ ላይ የተቃራኒ ቡድኑ አል ሸባብ ደጋፊዎች ተጨዋቹን ለማናደድ የሊዮኔል ሜሲን ስም እያነሱ ሲዘምሩ ለነበሩ ደጋፊዎች አስነዋሪ ያልተገባ ምልክት አሳይቷል ተብሏል።
ይህንን ተከትሎም ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎችን በምልክት በመዝለፍ ምርመራ እንደተከፈተበት ይታወቃል።
የሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ክርስቲያኖ ሮናዶ ቀርቦ ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ መጥራቱም ተነግሯል።
የሳዑዲ አል ሪያድ ጋዜጣ ምንጮች እንደተናሩት ከሆን፤ ሮናልዶ የቅጣት ውሳኔው በሚተላፍበት ወቅት በስፍራው በመገኝት ሂደቱን ተከታትሏል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚሁ ወቅት በሰጠው ማብራሪያም፤ ምንም አይነት የሰውን ሞራል የሚነካ ተግባር አለመፈጹም በመግለጽ የቀረበብት ክስ አስተባብሏል።
ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ “ያደረግኩት እንቅስቃሴ እና ያሳየሁት ምልክት ጥንካሬን እና ድልን ይገልፃል እንጂ አሳፋሪ አይደለም፤ ይህንን አይነቱን የደስታ አገላለጽ በአውሮፓም ለምደነዋል” ብሏል።
ሮናልዶ የቀረበበትን ክስ ቢያስተባብልም ከሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅጣት ግን ማምለጥ አልቻለም ነው የተባለው።
ሮናልዶ ላይ የተላፉት ቅጣቶች ምንድን ናቸው?
የሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን እና የስነ ምግባር ኮሚቴ፤ ክርስቲያኖ ሮናዶ የአልሸባብ ክልብ ደጋዎችን በመስደብ የሀገሪቱን የእግር ኳ መተዳደሪያ ደብን አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 1 ተላልፏል ብሏል።
ይህንን ተከትሎም የዲሲፕሊን እና የስነ ምግባር ኮሚቴው ክርስቲያኖ ሮናልዶን የአንድ ጨዋታ ቅጣት እ የ10 ሺህ የሳዑዲ ሪያል ቅጣት አሳልፎበታል ነው የተባለው።
በተጨማሪም ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለአልሸባብ ክለብ 20,000 የሳዑዲ ሪያል እንዲከፍል ተወስኗል።
ቅጣቱን ተከትሎም ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሳዑዲ ሊግ 22ኛ ሳምንት ክለቡ አል ናስር ከአል ሃዛም ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ይሆናል።