የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለእስራኤል የ4 ቢሊዮን ወታደራዊ እርዳታ በአስቸኳይ እንዲደርሳት ማዘዛቸውን ገለጹ
ፔንታጎን ባለፈው አርብ እለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለእስራኤል ሶስት ቢሊዮን ዋጋ ያላቸው ቦምቦች፣ ማፍረሻ ኪቶችና ሌሎች መሳሪያዎች ሽያጭ ማጽደቁን አስታውቋል

የትራምፕ አስተዳደር በቅርብ ሳምንታት ውስጥ መሳሪያዎችን በፍጥነት ለእስራኤል ለመሸጥ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን ሲጠቀም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እስራኤል የአራት ቢሊዮን ዋጋ ያለው ወታደራዊ እርዳታ በፍጥነት እንዲደረሳት በሚያስችል ትዕግሥት ላይ መፈረማቸውን ተናግረዋል።
ባለፈው ጥር ወር መጨመረሻ ወደ ኃይትሀውስ የገባው የትራምፕ አስተዳደር ለእስራኤል 12 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ሩቢዮ "አሜሪካ ለእስራኤል ደህንነት የገባችውን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ሁሉንም አማራጮች ትጠቀማለች" ሲሉ አክለዋል።
ሩቢዮ ወታደራዊ እርዳታው ከሀማስ ጋር አስተማማኝ ያልሆነ ተኩስ አቁም ውስጥ ላለችው ለመካከለኛው ምስራቋ አጋር በፍጥነት እንዲደርስ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣናቸውን መጠቀማቸውን ገልጸዋል።
ፔንታጎን ባለፈው አርብ እለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለእስራኤል ሶስት ቢሊዮን ዋጋ ያላቸው ቦምቦች፣ ማፍረሻ ኪቶችና ሌሎች መሳሪያዎች ሽያጭ ማጽደቁን አስታውቋል።
አስተዳደሩ የአስቸኳይ ሽያጩን ጉዳይ ለኮንግረሱ አሳውቋል። የትራምፕ አስተዳደር በቅርብ ሳምንታት ውስጥ መሳሪያዎችን በፍጥነት ለእስራኤል ለመሸጥ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን ሲጠቀም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የቀድሞው ፕሬዝደንት ባይደን አስተዳደር ያለኮንግረስ ግምገም የጦር መሳሪያዎችን ለእስራኤል ለመሸጥ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን ይጠቀም ነበር። ባለፈው ሰኞ እለት የትራምፕ አስተዳደር እስራኤልን ጨምሮ የአሜሪካ አጋሮች የአሜሪን መሳሪያ በመጠቀም አለምአቀፍ ህግ እንዳይጥሱ የሚከለክለውን በባይደን ዘመን የነበረውን ህግ ሰርዞታል።
ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ የተፈረመው የእስራኤል-ሀማስ ተኩስ አቁም ስምምነት ለ15 ወራት የዘለቀውን ጦርነት እንዲቆም፣ 33 ታጋቾች እንዲለቀቁና 2000 ገደማ ፍልስጤማውያን እስረኞች እንዲለቀቁ አስችሏል። የመጀመሪያ ዙር ተኩስ አቁም ሊጠናቀቅ ሰአታት ሲቀሩት እስራኤል አሜሪካ ያቀረበችውን ጊዜያዊ የረመዳን ጾም ተኩስ አቁም መቀበሏን አስታውቃለች።