የግል ፍላጎቱን ለማርካት ሲል በልጁ ላይ ያደረገው ድርጊት ትዳሩ እንዲፈርስ ምክንት ሆኗል
የማራቶን ውድድር ለመሳተፍ ሲል ልጁን ለሰዓታት መኪናው ውስጥ ያስቀመጠው አባት፡፡
በሩቅ ምስራቋ ቻይና አንድ መሮጥ የሚወድ አባት በልጁ ላይ ደረገው ድርጊት ውግዘትን እያደረሰበት ይገኛል፡፡
በደቡባዊ ቻይና ሁናን ግዛት የሚኖረው ይህ አባት ባለትዳር እና የአንድ ሴት ልጅ አባትም ሲሆን በሚስቱ አነሳሽነት ነበር መሮጥ የጀመረው፡፡
ይህ አባወራም ቀስ በቀስ ለሩጫ ያለው ፍቅር እየጨመረ መጥቶ በማራቶን ውድድር ላይ እስከመሳተፍ ይደርሳል፡፡
የዚህ ሰው ሚስትም ስራ እንደሚበዛባት እና ሴት ልጃቸውን ባልየው እንዲያዝ በተስማሙት መሰረት ያሰበችውን ጉዳ ለመፈጸም ከቤት ትወጣለች፡፡
የአምስት ዓመት እድሜ ያላት ሴት ልጃቸውን እንዲጠብቅ ሀላፊነት የተሰጠው ባልም ልጁን በተሸከርካሪ ውስጥ በማስቀመጥ እና በመዝጋት የማራቶን ውድድሩን ይሳተፋል፡፡
ለ75 ዓመታት በትዳር የኖሩት ጥንዶች በሰዓታት ልዩነተ ህይወታቸው አልፏል
ሚስትም ሴት ልጃቸው ለስድስት ሰዓት ያህል ተሸከርካሪ ውስጥ እንደቆየች ካወቀችበት በኋላ በባሏ ድርጊት መበሳጨቷን ገልጻ ትዳሩ እንዲፈርስ ማድረጓ ተገልጿል፡፡
ባሌ ከልጁ ይልቅ ለምን ቅድሚያ እንደሚሰጥ ካወቅሁ በኋላ አብሬው መኖር አልፈለኩም ስትል በማህበራዊ ትስስር ገጻ ላይ ያሰፈረችው መልዕክት ለበርካቶች ተዳርሷል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በባልየው ድርጊት ያዘኑ ቻይናዊን የልጅቷን አባት እያወገዙ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ በመጻፍ ላይ ሲሆኑ ውግዘት እየደረሰበት ያለው ባልም እኔ 1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ከሮጥኩ በኋላ ወደ ልጄ ተመልሻለሁ ሲል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡