ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ለመነጋገር በሬ ክፍት ነው አለች
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፑቲን ጦርነቱ የሚያበቃበትን መንገድ እየፈለጉ ከሆነ ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን ተናግረዋል
በሩሲያ የተጠቃለሉ ግዛቶችን አሜሪካ እውቅና አልሰጥም ማለቷ ጦርነቱን የሚያቆምበትን መንገድ ፍለጋ እያደናቀፈ ነው ተብሏል
ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ለመነጋገር በሬ ክፍት ነው አለች
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ዙሪያ "ለመደራደር ዝግጁ ናቸው" ተብሏል። ነገር ግን ምዕራባውያን የሞስኮን ጥያቄ መቀበል አለባቸው ብሏል ክሬምሊን።
የክሬምሊን መግለጫ የመጣው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፑቲን ጦርነቱን የሚያበቃበትን መንገድ እየፈለጉ ከሆነ ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን ከተናገሩ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
ባይደን እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሐሙስ ዕለት በዋይት ሀውስ ከተነጋገሩ በኋላ፤ ሩሲያ በዩክሬን ላደረገችው ድርጊት ተጠያቂ እንደምትሆን ተናግረዋል።
ነገር ግን ፕሬዝዳንት ባይደን በፑቲን አቋም “ምንም አይነት የለውጥ ምልክት” እንዳላዩ በመግለጽ ከሞስኮ ጋር ሰላም ለማውረድ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።
ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ የካቲት ወር ወዲህ ባይደን ከፑቲን ጋር በቀጥታ አልተነጋገሩም።
ሞስኮ ለባይደን በሰጠችው ምላሽ በዩክሬን ጉዳይ ለመነጋገር በሬ ክፍት ነው ብላለች።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ “የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጥቅማችንን ለማረጋገጥ ሁልጊዜም ለድርድር ፈቃደኛ ናቸው” ብለዋል።
ፔስኮቭ አሜሪካ በሩሲያ የተጠቃለሉ ግዛቶችን እውቅና አልሰጥም ማለቷ ጦርነቱን የሚያቆምበትን መንገድ ፍለጋ እያደናቀፈ ነውም ብለዋል።
ሞስኮ ቀደም ሲል የኔቶ ምስራቃዊ መስፋፋትን ጨምሮ ከፍተኛ የደህንነት ዋስትናዎችን እንደምትፈልግ ተናግራ ነበር።
ፑቲን ለጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልስ በስልክ በዩክሬን ላይ ያለው የምዕራቡ ዓለም መስመር “አፍራሽ ነው” በማለት በርሊን አካሄዷን እንደገና እንድታስብ አሳስበዋል ሲል ክሬምሊን ተናግሯል።
በመሪዎች ንግግር ላይ የሾልስ ቃል አቀባይ “ቻንስለሩ የሩሲያን የአየር ጥቃት በሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ አውግዘዋል እናም ለጦርነቱ የሩሲያ ወታደሮችን መውጣትን ጨምሮ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል” ብለዋል።
ፑቲን ትጥቅ ለማስፈታት እና ዩክሬንን ለመከልከል "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" በመጀመራቸው ምንም አይነት ጸጸት እንደሌለባቸው ተናግረዋል።
ኪየቭ የመጨረሻው የሩሲያ ወታደር ከግዛቷ እስኪወጣ ድረስ እንደሚዋጋም ተናግራለች።