ሩሲያ በዩክሬን ላደረሰችው ጉዳት 600 ቢሊዮን ዩሮ ካሳ መክፈል እንዳለባት የአውሮፓ ህብረት ገለጸ
የአውሮፓ ህብረት የሩሲያ የጦር ወንጀሎችን ለመዳኘት ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ሀሳብ አቀረበ
የፍርድ ቤቱ አደረጃጀት ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ወይም ቅይጥ የሚለው እስካሁን አልታወቀም።
ሩሲያ በዩክሬን ላደረሰችው ጉዳት 600 ቢሊዮን ዩሮ ካሳ መክፈል እንዳለባት የአውሮፓ ህብረት ገለጸ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌየን በዩክሬን የተፈጸሙ የሩስያ የጦር ወንጀሎችን ለመዳኘት ልዩ ፍርድ ቤት ለማቋቋም ጥያቄ አቅርበዋል።
"የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ሞትን፣ ውድመትንና ሊነገር የማይችል ስቃይ አስከትሏል በማለት ቮን ደር ሌየን በመግለጫቸው ተናግረዋል።
"ሩሲያ በሉዓላዊ ሀገር ላይ ለፈጸመችው የጥቃት ወንጀል ጨምሮ ለአሰቃቂ ወንጀሎች መክፈል አለባት" ብለዋል።
"ለዚህም ነው የአለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መደገፍን ስንቀጥል በተባበሩት መንግስታት የተደገፈ ልዩ ፍርድ ቤት ለማቋቋም እና የሩስያን የጥቃት ወንጀል ለመመርመር እና ለመክሰስ ሀሳብ እያቀረብን ያለነው" በማለት አስረድተዋል።
እንደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ወይም እንደ ቅይጥ የሚለው ሊፈጠር ይችላል ተጨባጭ ህጎች በዩክሬን የህግ ስርዓት ላይ የተመሰረቱ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።
አሰራሮቹ አለም አቀፍ ህጎችን የሚከተሉ ናቸው ሲል የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
“በሁለቱም ጉዳዮች ጊዜያዊም ሆነ ድብልቅ ፍርድ ቤት የተባበሩት መንግስታት ድጋፍ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
ቮን ደር ሌየን የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንደሚሰራ እና ለዚህ ፍርድ ቤት የሚቻለውን ሰፊ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚጥር ቃል ገብተዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላደረሰችው ጉዳት 600 ቢሊዮን ዩሮ የሚገመት ካሳ መክፈል አለባት ሲሉም ተናግረዋል።
ቮን ደር ሌየን አክለውም "እኛ ደግሞ ሩሲያ መክፈል የሚያስችል መንገድ አለን" ብለዋል። የ 300 ቢሊዮን ዩሮ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ክምችት እና 19 ቢሊዮን ዩሮ የሩሲያ ከበርቴዎች ገንዘብ በአውሮፓ ህብረት የታገደ ሲሆን፤ ገንዘቡ ለዚህ ዓላማ ጥቅም ላይ ይውላል ብለዋል። ሆኖም የዩክሬን መልሶ ግንባታ በታገዱ የሩስያ ንብረቶች ለመደገፍ ለአውሮፓ ህብረት ህጋዊ ራስ ምታት እንደሚከተለው ፖለቲኮ ዘግቧል።