ከኩባንያው ጋር በሽርክና ለመስራት የተዋዋለው የሩሲያው ጋዝ የተሰኘው ድርጅት 208 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ኪሳራ ገጥሞኛል ብሏል
የሩስያ ፍርድ ቤት የጀርመኑን ቮልስዋገን ንብረቶችን አገደ
የሩስያ ፍርድ ቤት በሩሲያ የሚገኙትን የቮልስዋገን ንብረቶችን ማገዱን ሮይተርስ የተመለከታቸው የፍርድ ቤት ሰነዶች አመልክተዋል።
ቮልስዋገን በዩክሬን በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በሞስኮ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ በሩሲያ ውስጥ ስራቸውን ካቆሙ የውጭ መኪና አምራቾች መካከል አንዱ ነው።
የቮልስዋገንን ተሽከርካሪዎች ለማምረት የተዋዋለው የሩሲያ የመኪና አምራች ጋዝ፤ ቮልክስዋገን በነሀሴ ወር ስምምነቱን ካቋረጠ በኋላ ስምምነትን በማፍረስ ጀርመናዊውን መኪና ሰሪ ከሷል።
ጋዝ ውሉ በመቋረጡ ኪሳራውን 207.79 ሚሊዮን ዶላር ገምቷል።
ቮልስዋገን ከሞስኮ በስተደቡብ ካሉጋ የሚገኘውን ዋናውን የሩሲያ ፋብሪካ ለመሸጥ እየሞከረ ነው ተብሏል።
በዓመት 225 ሽህ ተሸከርካሪዎችን የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው ከመጋቢት 2022 ጀምሮ ተዘግቷል።