ባክሙት ለሩሲያ እና ዩክሬን ለምን አስፈላጊ ሆነች?
ከጦርነቱ በፊት 70 ሽህ የሚጠጉ ሰዎች ይኖሩባት የነበረው ባክሙት ጥቂት ሽህዎችና ፍርስራሿ ብቻ ቀርቷል ተብሏል
ወታደራዊ ተንታኞች ባክሙት ስልታዊ ጠቀሜታ አላት ብለዋል
በምስራቅ ዩክሬን የምትገኘው አነስተኛ የኢንዱስትሪ ከተማ ባክሙት ከሰባት ረጅም ወራት በላይ በሩሲያ ጦር ስትደበደብ ቆይታለች።
ምክትል ከንቲባዋ ኦሌክሳንደር ማርቼንኮ፤ ውሃ፣ ጋዝ እና ኃይል በሌለባቸው መሬት በተቀበሩ መጠለያዎች ጥቂት ሽህ ንጹሀን ዜጎች ቀርተዋል።
"በዚህ ጦርነት ውስጥ ያልተነካ አንድም ህንጻ የለም። ከተማዋ ልትፈርስ ተቃርባለች" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ታዲያ ለምንድነው ሩሲያ እና ዩክሬን በፍርስራሽ ክምር ላይ ይህን ያህል የሚዋጉት? ጦርነቱ ረጅም ጊዜ በዘለቀባት ከተማ ለማጥቃት እና ለመከላከል ለምን የበርካታ ወታደሮችን ህይወት ይጠፋል?
ወታደራዊ ተንታኞች ባክሙት "ትንሽ" ስልታዊ ጠቀሜታ አላት ይላሉ።
ሆኖም ከተማዋ የጦር ሰፈር ወይም የትራንስፖርት ማዕከል አሊያም የህዝብ ዋና ማዕከል አይደለችም።
ከጦርነቱ በፊት ወደ 70 ሽህ የሚጠጉ ሰዎች በከተማዋ ይኖሩ ነበር። ከተማዋ በይበልጥ የምትታወቀውም በጨውና በጂፕሰም ማዕድን ማውጫዎቿ እና በትላልቅ የወይን ፋብሪካዎች ነበር።
አንድ የምዕራባውያን ባለስልጣን እንዳስቀመጡት ባክሙት "በአንድ ሽህ 200 ኪሎ ሜትር የግንባር መስመር ላይ ያለች አንድ ትንሽ የታክቲክ ክስተት" ናት።
ሆኖም ሩሲያ ከተማዋን ለመያዝ ከፍተኛ ወታደራዊ ሀብቶችን እያሰማራች ነው።
የምዕራባውያን ባለስልጣናት እስካሁን በባክሙት እና አካባቢው ከ20 ሽህ እስከ 30 ሽህ የሚደርሱ የሩስያ ወታደሮች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ብለው ይገምታሉ።
ለሞስኮ በዩክሬን ላሉ የሩሲያ ደጋፊዎች ባክሙትን መያዝ ትልቅ ፕሮፓጋንዳ መሆኑ ተነግሯል።
የሩሲያ አዛዦች በወታደራዊ ምክንያቶች ባክሙትን መውሰድ ይፈልጋሉም የተባለ ሲሆን፤ ለተጨማሪ የግዛት ጥቅማጥቅሞች መነሻ እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋሉ ተብሏል።
የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከያ ሚንስቴር ከተማዋን መያዝ ሩሲያ በአካባቢው ላሉ ትላልቅ ከተማዎች መልዕክት አለው ብሏል።
በዩክሬን በኩል ደግሞ ባክሙትን ወታደሮች እያለቁባት ለመከላከሏ ስልታዊ አላማው የሩሲያን ጦር ማዳከም እንደሆነ ቢቢሲ ጠቅሷል
የኔቶ ምንጮች እንደሚገምቱት በባክሙት ውስጥ "ለአንድ ዩክሬናዊ አምስት ሩሲያዊያን እየሞቱ ነው" ሲልም ዘገባው አትቷል።