ፖለቲካ
ሩሲያ የሳኡዲ አረቢያው ስብሰባ "ያልተሳካ ሙከራ" ነው አለች
ሩሲያ በሳኡዲ አረቢያ በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ጉዳይ የተደረገው ስብሰባ "ያልተሳካ ሙከራ" ነው ብላዋለች
ዩክሬን ይህ ስብሰባ ግጭቱን በሰላም ለመቋጨት እንደሚያግዝ ገልጻለች
ሩሲያ በሳኡዲ አረቢያ በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ጉዳይ የተደረገው ስብሰባ "ያልተሳካ ሙከራ" ነው ብላዋለች።
ሩሲያ ስብሰባው በደቡብ ንፍቀ ክበብ ያሉ ሀገራት ከዩክሬን ጋር ለማስለፍ የተደረገ ሙከራ መሆኑን እና አለመሳካቱን ተናግረዋል።
ነገርግን ዩክሬን ይህ ስብሰባ ግጭቱን በሰላም ለመቋጨች ስኬታማ እንደሆነ የዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በስብሰባው ዩክሬን እና ምዕራባውያን የተሳተፉ ሲሳተፉ ሩሲያ ግን በስበስባው እንድትሳተፍ አልተጋዘችም።ሩሲያ የስብባው አለማ ምን እንደሆነ ማወቅ እንደምትፈልግ ስትገልጽ ነበር።
በዚህ ስብሰባ ላይ ቻይናን፣ ህንድን እና አሜሪካን ጨምሮ 40 ሀገራት መሳተፋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዩክሬን ስብሰባው ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን እንድትለቅ አለምአቀፍ ድጋፍ የሰበሰበችበት ነው ተብሏል።
ኘሬዝደንት ዘለንስኪ በዚህ ጉዳይ አለም አቀፍ ስብሰባ እንዲደረግ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ቀደም ሲል ከዩክሬን ጋር የሚደረግ ንግግርን እንደማይቃወሙት ተናግረው ነበር። ነገርግን ንግግር ለመጀመር መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተችው ዩክሬን ጥቃቱን ማቆም እንዳለባት ተናግረዋል።