የሩሲያ ጦር ከአንድ ወር በፊት አቭዲቭካ የተሰኘችውን መንደርን ተቆጣጥሯል
ሩሲያ ቶቴንክ የተሰኘችውን የዩክሬን መንደር ተቆጣጠረች።
ሶስተኛ ዓመቱን የያዘው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን ሩሲያ በምስራቃዊ ዩክሬን በኩል መንደሮችን እየተቆጣጠረች መሆኗን ገልጻለች።
እንደ ዶቸቪሌ ዘገባ የሩሲያ ጦር ቶተንኬ የተሰኘችውን መንደር መቆጣጠሩን አስታውቋል።
የሩሲያ ጦር ከሁለት ቀን በፊት ኦርሊቭካ የተሰኘችውን መንደር ከዩክሬን ጦር መንጠቁን መግለጹ አይዘነጋም።
ከአንድ ወር በፊት የሩሲያ ጦር አቭዲቭካ የተሰኘችውን መንደር ከብዙ ወራት ውጊያ በኋላ መቆጣጠሩን አስታውቆ ነበር።
ዩክሬን በበኩሏ ጦሯን ከአቭዲቭካ ስልታዊ ማፈግፈግ በሚል ከስፍራው ማስወጣቷን በወቅቱ ገልጻለች።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የርቀት ጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎች እንዲሰጧት ጥሪ አቅርባለች።
በተለይም ዩክሬን ከሩሲያ የሚደርስባትን የሚሳኤል ጥቃት ለማክሸፍ እና የመልሶ ማጥቃት ለመክፈት የጦር መሳሪያዎች እንዲሰጧት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ተናግረዋል።
ሀንጋሪ እና ስሎቫኪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎቻቸውን እንደማይሰጡ ሲናገሩ ዴንማርክ ያላትን ጦር መሳሪያ ሁሉ ለዩክሬን እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
ይህ በዚህ እንዳለም ፈረንሳይ ሁለት ሺህ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን እንደምትልክ ያስታወቀች ሲሆን ሩሲያ ፓሪስን አስጠንቅቃለች።