ሩሲያ ከቅርቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ወታደሮችን ቀጥራለች
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በያዝነው የፈረንጆቹ 2024 መጨረሻ ላይ ሁለት ግዙፍ ጦሮች እንደምታቋቁም አስታውቃለች።
የመከላከያ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ፤ የሩሲያ ጦር የዩክሬን ኃይሎቸን ወደኋላ እንዲያፈገፍጉ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሰርጌይ ሾይጉ ለከፍተኛ ጄኔራሎች እንደተናገሩት "የሩሲያ ወታደሮች ጠላትን ከቦታቸው በማስወጣት አካባቢውን መቆጣጠራቸውን ቀጥለዋል" ብለዋል።
አሜሪካ እና አጋሮቿ የሩሲያ ጦር እያስመዘገበ ያለው ስኬት በእጅጉ እንዳሳሰባቸውም ነው የመከላከያ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
የሩሲያ ጦርን በአንድነት የማደረጃቱ ስራ እንደሚቀጥል የተናገሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ፤ ይህም የጠላት ኢላማዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ያጠናክራል ብለዋል።
በዚህም መሰረት በቀርቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ወታደሮችን የቀጠረችው ሩሲያ ሁለት አዳዲስ ግዙፍ ክፍለ ጦሮችን እንደምታቋቁም አስታውቀዋል።
አዳዲሱቹ ክፍለ ጦርች 30 የተለያዩ አደረጃጀቶች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን፤ ይህም 14 ዲኒዥን እና 16 ብርጌዶች የተቃወረ እንደሚሆን ነው የተገለጸው።
ከሩሲያ ምርጫ ጋር በተያያዘም የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሾይጉ በሶስት ቀናቱ ምርጫ ሩሲያ ከዩክሬን የተቃጡ በርካታ ጥቃቶችን አምክናለች ብለዋል።
በምርጫው ቀናት ሩሲያ 419 የዩክሬን ድሮኖችን እና 67 ከዩክሬን የተተኮሱ ሮኬቶች መትታ መጣሏንም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።
ዩክሬን በምርጫው ቀን ሩሲያ ላይ ጥቃት መክፈቷን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ፑቲን ዩክሩን ትቃጣለች ሲሉ መዛታቸውም አይዘነጋም።