አዲስ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና ተሰጠው
የኤች.አይ.ቪ መከላከያ ክትባቱ በየሁለት ወር ልዩነት የሚሰጥ ነው ተብሏል
ክትባቱ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች መልካም ዜና ነው ተብሏል
የዓለም ጤና ድርጅት ለአዲስ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ ክትባት እውቅና መስጠጡ ተሰምቷል።
ድርጅቱ በወራት ሉዩነት በክትባት መልክ የሚሰጠው የየኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቅዷል።
ይህም ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ ከሚወሰዱ የመከላከያ እርምጃዎች አካል እንደሆነም ተነግሯል።
በአንድ ጊዜ ክትባት ለረጅም ጊዜ እንደሚያገለግል የተነገረው መድሃኒቱ፤ በሰዎች ሰውነት ውስጥ በመግባት የመከላከል ስራን ይሰራል ተብሏል።
ክትባቱ በዙር የሚሰጥ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዙር በእየአራ ሳምንታት ልዩነት ሁለት ጊዜ ይሰጣል ተብሏል።
በመቀጠልም ክትባቱ በየስምት ሳምት አሊያም ሁለት ወር ልዩነት በቋነት እየተሰጠ ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ ለመከላከል ይረዳል።
ክትባቱ ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ነው የተባለ ሲሆን፤ ክትባቱ ለተጠቃሚዎች መድረስ እንዳልጀመረም ነው የተገለፀው።
ለቨይረሱ ተጋላጭ የሆኑ በርካታ ሰዎች አሁን ላይ በየእለቱ የሚወሰድ የመከላከያ እንክብል በመዋጥ ላይ ይገኛሉ።
ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል እውቅና ማግኘቱ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች መልካም ዜና ነው ተብሏል።
ከዚህ ቀደም አሜሪካ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ ክትባቶችን ለዜጎቿ ልትሰጥ እንደምትሰጥ አስተውቃ ነበር።
‘አፕሪቱድ’ ወይም ‘ካቦቲግራቪየር’ የተሰኘው ይህ ክትባት በተለይም ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ እና ከ35 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ላላቸው ወጣቶች እንዲሰጥ አሜሪካ ማጽደቋ ይታወሳል።
በገዳይነቱ 38 ዓመታትን ያስቆጠረው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በዓለም ዙሪያ 37 ሚሊዮን ሰዎችን የገደለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 25 ሚሊዮን ያህሉ አፍሪካዊያን ናቸው።
በዓለማችን በየዓመቱ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ የሚያዙ ሲሆን በ2020 ዓመት ብቻ ከ680 ሺህ በላይ ዜጎች በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡