በምዕራቡ ዓለም የመከላከያ መሪዎች ስብሰባ ዩክሬን ታንክ እንደሚቀርብላት ትጠብቃለች
የምዕራባዊያን የጀርመን ስጋት ከመሳሪያ አቅርቦቱ በኋላ ሩሲያ ምን ልታደርግ ትችላለች የሚለው ላይ የተንጠለጠለ ነው ብለዋል
ዩክሬን እና ሩሲያ ለጦርነቱ በዋነኛነት በሶቭየት ዘመን በተሰሩ "ቲ-72" የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታንኮች ወድመውባቸዋል ተብሏል
በምዕራቡ ዓለም የመከላከያ መሪዎች ስብሰባ ዩክሬን ታንክ እንደሚቀርብላት ትጠብቃለች።
የምዕራባዊያን አጋር ሀገራት የጀርመን ስጋት ከመሳሪያ አቅርቦቱ በኋላ ሩሲያ ምን ልታደርግ ትችላለች የሚለው ላይ የተንጠለጠለ ነው ብለዋል።
ዩክሬን እና ሩሲያ ለጦርነቱ በዋነኛነት በሶቭየት ዘመን በተሰሩ "ቲ-72" የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታንኮች ወድመውባቸዋል ተብሏል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘሌንስኪ እንዳሉት መንግስታቸው የሩስያን ጦር በዘመናዊ የጦር ታንኮች መመከት በሚችባልበት ሁኔነታ ላይ ውሳኔ እየጠበቁ ነው።
ዘለንስኪ የኔቶ መከላከያ መሪዎች እና ሌሎች ሀገራት መከላከያ አዛዦች በታንክ አቅርቦት ላይ “ጠንካራ ውሳኔዎችን” ያሳልፋሉ ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
"እኛ በእውነቱ ከአውሮፓ ዋና ከተማ ውሳኔን እየጠበቅን ነው። ታንኮችን በተመለከተ የተዘጋጁትን የትብብር ሰንሰለቶች ያነቃቃል" ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል።
በጀርመን ራምስቴይን አየር ማረፊያ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ስብሰባ ከዛሬ 11 ወራት በፊት በተቀሰቀሰው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ በተከታታይ ከተካሄዱ ስብሰባዎች አንዱ ነው።
የጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ በተለይም በአውሮፓ የሚገኙ ጦር ኃይሎች ስለሚጠቀሙበት የጀርመን "ሊዮፓርድ ሁለት ታንኮች" ውይይት የሚደረግበት ነው።
በርሊን ታንኮቹን ወደ ውጭ ለመላክ በሚደረገው ማንኛውም ውሳኔ ላይ ድምጽን በድምጽ የመጣል ስልጣን ያላት ሲሆን፤ የመራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልስ መንግስት ሩሲያን እንዳያበሳጭ በመፍራት ይህንን ፈቃድ ለመስጠት እያመነታ ይመስላል ተብሏል።
የምዕራባዊያን አጋር ሀገራት የጀርመን ስጋት ሩሲያ ምን ልታደርግ ትችላለች የሚለው ላይ የተንጠለጠለ ነው ብለዋል። በተለይም የጦር መሳሪያ ዝውውር ግጭቱን የሚያራዝም እና በዩክሬን ውስጥ ስቃይ እንደሚጨምር ስጋት አድሮባታል ነው የተባለው ።
ዩክሬን እና ሩሲያ ሁለቱም ሀገራት ለጦርነቱ በዋነኛነት በሶቭየት ዘመን በተሰሩ "ቲ-72" የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታንኮች ወድመውባቸዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የምዕራባውያን ሀገሮች ለዩክሬን የማያቋርጥ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ሰጥተዋልም።