የሩሲያ ቲያትር ዳሬክተር እና የተውኔት ጸኃፊ በሽብርተኞች መዝገብ ውስጥ ተካተቱ
በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ባይባሉም፣ ሀብት ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ይደረጋል
የሩሲያ መንግስት የሩሲያ ቲያትር ዳይሬክተርን እና የተውኔት ጸኃፊን "በሽበርተኞች እና በአክራሪዎች" ዝርዘር ውስጥ አካተተ
የሩሲያ መንግስት የሩሲያ ቲያትር ዳይሬክተርን እና የተውኔት ጸኃፊን "በሽበርተኞች እና በአክራሪዎች" ዝርዘር ውስጥ አካተተ።
በይፋ "በሽብርተኞች እና አክራሪዎች" መዝገብ ውስጥ የተካተቱት የሩሲያ የቲያትር ዳይሬክተር ዘንያ በርኮቪች እና ጸኃፈ ተውኔት ስቬትላና ፔትሪቹክ የሚመሰረትባቸውን ክስ እየጠበቁ ነው።
ሁለቱ ግለሰቦች የተያዙት ባለፈው አመት ነበር። ግለሰቦቹ በመዝገቡ የተካተቱት የሩሲያ ሴቶች እስላማዊ ታጣቂዎችን ሲያገቡ የሚሳይ ቲያትር በመስራታቸው ነው ተብሏል።
"የሽብርተኞች እና አክራሪዎች" መዝገብ በኦንላይ የሚታተም ሲሆን መንግስታዊው ሮዝፊንሞኒተሪንግ የተባለው ኤጀንሲ ያስተዳድረዋል።
በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ባይባሉም፣ ሀብት ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ይደረጋል።
የ38 አመቷ በርኮቪች እና የ43 አመቱ ፔትሪቹክ በመንግስት ላይ በማሴር በተለይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ባጠናከረችው ዘመቻ ሰለባ ከሆኑ በሽዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች መካከል ናቸው።
ክሬሚሊን ስሁለቱ ግለሰቦች አስተያየት ባይሰጥም፣ ሩሲያ ከምዕራባውያን የህልውና ስጋት ስላጋጠማት ህጓን አጠናክራ ራሷን ትከላከላለች ብሏል።
'ፊነስት ዘብራይት ፋልኮን' የተሰኘው ቲያትር በበርኮቪች ተጽፎ በዳሬክተሩ ፔትሩቺክ አማካኝነት በ2020 ነበር ለእይታ የቀረበው።