ዩክሬን በሩሲያ የጦር ሰፈር ላይ ባደረሰችው ጥቃት 6 የጦር አውሮፕላኖችን አወደምኩ አለች
ይህ የጦር ሰፈር በግንባር ውጊያ የሚሳተፉት ሱ-24፣ሱ-24ኤም እና ሱ-34 ጄቶች ማረፈያ ቦታ ነው
ዩክሬን በደቡብ ሩሲያ ባካሄደችው የድሮን ጥቃት በሮስቶብ የጦር ሰፈር የነበሩ ስድስት የጦር አውሮፕላኖችን መውደማቸውን ገልጻለች
ዩክሬን በሩሲያ የጦር ሰፈር ላይ ባደረሰችው ጥቃት ስድስት የጦር አውሮፕላኖችን አወደምኩ አለች።
ዩክሬን በደቡብ ሩሲያ ባካሄደችው የድሮን ጥቃት በሮስቶብ የጦር ሰፈር የነበሩ ስድስት የጦር አውሮፕላኖችን መውደማቸውን ገልጻለች።
ከአውሮፕላኖቹ በተጨማሪ ስምንት ጀቶች መጎዳታቸውን እና በቦታው የነበሩ 20 ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ቢቢሲ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
እንዘገባው ከሆነ ይህ የጦር ሰፈር በግንባር ውጊያ የሚሳተፉት ሱ-24፣ሱ-24ኤም እና ሱ-34 ጄቶች የሚነሱበት እና የሚያርፉበት ቦታ ነው።
ሩሲያ በጦር ሰፈሩ ላይ ደርሷል ስለተባለው ጥቃት ያለችው ነገር የለም። ነገርግን የሩሲያ ባለስልጣናት ከ40 በላይ የሩሲያ ድሮኖች ወደ ከዩክሬን ጋር ድንበርተኛ ወደሆነው ክልል ኢላማ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የመከላከያ ሚኒስቴሩ እንደገለፈው ሳራቶቭ፣ ኩርስክ፣ ቤልጎሮድ እና ክራስኖዳር ግዛቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል። ሚኒስቴሩ ሁሉም ድሮኖች ተመትተው ወድቀዋል ብሏል።
የሮስቶብ ገዥ የሆኑት ቫስሊ ጎሉቤቭ ግን በቴሌግራም ገጻቸው እንዳሉት በሮስቶቭ ሞሮዞቭስክ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ጣቢያ ላይ በደረሰ ጥቃት 600 ሰዎች የኃይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል።
ገዥው በጥቃቱ ባለ16 ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ ላይም ጉዳት ደርሶበታል ብለዋል።
ዩክሬን በቅርቡ በሩሲያ ውስጥ በወታደራዊ እና በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የምታደርሰውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላቀታለች።
ጦሯ የተተኳሽ እጥረት እንዳጋጠመው በተደጋጋሚ የገለጸች ዩክሬን በዚህ አመት በሀገር ውስጥ አንድ ሚሊዮን ድሮን ለማምረት አቅዳለች።
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ያሉ እና ሙሉ ለሙሉ እስከምትቆጣጠር ድረስ ሁለት አመት ያለፈው ጦርነት እንደሚቀጥል መግለጿ ይታወሳል።