ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ግንባር ከፍተኛ ጫና እያሳደረች መሆኑን የዩክሬን ጦር አዛዥ ገለጹ
አዛዡ እንደገለጹት በምስራቅ ዩክሬን ግንባር ያለው ውጊያ በተለይም ፕሬዝደንት ፑቲን በድጋማ መመረጥ በኋላ ጠንክሯል
የዩክሬን ጦር አዛዥ ሩሲያ ከባክሙት በምዕራብ አቅጣጫ ያሉ መንደሮችን ለመቆጣጠር እየጣረች ነው ብለዋል
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ግንባር ከፍተኛ ጫና እያሳደረች መሆኑን የዩክሬን የጦር አዛዡ ገለጹ።
የዩክሬን ጦር አዛዥ በዛሬው እለት እንደገለጹት ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን በብረት ለበስ ተሽከርካሪ በመታገዝ ከባክሙት በምዕራብ አቅጣጫ ያሉ መንደሮችን ለመቆጣጠር እየጣረች ነው።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ሁለት አመት ካስቆጠረ በኋላ ጀነራል ኦሌክሳንደር ሲይርስኪ ያወጡት መግለጫ ኪቭ ችግር ውስጥ መሆኗን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ዩክሬን በተስፋ እየጠበቀችው ያለው የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እስካሁን በአሜሪካ ኮንግረስ ሊጸድቅ አልቻለም።
ወቅቱ ደረቅ እና ሞቃት መሆኑ የሩሲያ ወታደሮች ታንክ እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የበላይየት እንደያዙ የተናገሩት ሲርስኪ ወደ ግንባር በመሄድ ሁኔታዎች ማረጋጋታቸውን ተናግረዋል።
አዛዡ እንደገለጹት በምስራቅ ዩክሬን ግንባር ያለው ውጊያ በተለይም ፕሬዝደንት ፑቲን በድጋማ መመረጥ በኋላ ጠንክሯል።
ፕሬዝደንት ፑቲን በድጋሚ መመረጣቸውን ተከትሎ ሩሲያ ሶስት ከፍተኛ የሚባሉ የአየር ጥቃት በመክፈት በዩክሬን የኃይል መሰረተልማት ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት አስከትለዋል።
የምዕራባውያን ወታደራዊ እርዳታ መዘግየት ዩክሬን ለአየር ጥቃት እንድትጋለጥ እና በጦር ሜዳም ብልጫ እንዲወሰድባት አድርጓል ተብሏል።
ዩክሬን በቅርቡ ምዕራባዊያን የአየር ጥቃት መከላከያ ሚሳይል እንዲሰጧት ተማጽናለች።
የሩሲያ ኃይሎች በምስራቅ እየተካሄደ ባለው ውጊያ ከፍተኛ ኪሳራ ቢገጥማቸው ድሎችን መቀዳጀታቸውን አዛዡ አምነዋል።
ሩሲያ በከፊሎ የተቆጣጠረቻቸውን አራት የዩክሬን ምስራቃዊ ግዛቶች ለመቅጣጠር በማለም ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች።