ሩሲያ የጀርመን አየር ሀይል አመራሮች በሚስጢር ያወሩትን ሰነድ ይፋ አደረገች
ጀርመን በበኩሏ በሩሲያ ይፋ የተደረገባት ወታደራዊ ሚስጢር እውነት መሆኑን አረጋግጣለች
የጀርመን ወታደሮች ዩክሬንን ስለሚረዱበት ሁኔታ የሚያትተው ሚስጢር ከሰሞኑ ይፋ መሆኑ ይታወሳል
ሩሲያ የጀርመን ከፍተኛ ወታደሮች በሚስጢር ያወሩትን ሰነድ ይፋ አደረገች፡፡
የጀርመን አየር ሀይል አመራሮች ዩክሬን በሩሲያ ላይ ስለምትሰነዝራቸው ጥቃቶች እና እነሱ ሊያደርጉት ስላሰቡት ድጋፎች ውይይት መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡
በሩሲያ ይፋ ሆኗል የተባለው ይህ ወታደራዊ ሚስጢር ጀርመንን ይስቆጣ ሲሆን የሀገሪቱ መራሔ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ጉዳዩ እንዲመረመር አዘው ነበር፡፡
በዚህም ምርመራ መሰረትም ወጣ የተባለው የጀርመን አየር ሀይል አመራሮች ውይይት እውነት መሆኑን ዶቸ ቪሌ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ በሩሲያ የስለላ ተቋም የፋ የሆነው የጀርመን አየር ሀይል የውይይት ቅጂ አዲቲንግ የተደረገ ይሁን አይሁን ግን ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግበት መታዘዙም ተገልጿል፡፡
የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር አባወጣው መግለጫ ባደረግነው ማጣራት መሰረት የአየር ሀይል ከፍተኛ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ስለ ዩክሬን ጦርነት የሚያወሩት መጠለፉን አረጋግጠናል፣ ከዚህ በላይ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ነገር ማለት አንችልም ሲል አስታወቋል፡፡
የጀርመን አየር ሀይል አዛዥን ጨምሮ ተሳትፈውበታል በተባለው በዚህ ውይይት ላይ ዩክሬን የክሪሚያ ድልድይን እንድትመታ ታውረስ ክሩዝ ሚሳኤል ልንሰጣት እንችላለን የሚለው ዋነኛው ነው፡፡
ጀርመን ከሩሲያ ጋር የቀጥታ ግጭት ውስጥ እንዳትገባ እኛ ለዩክሬን መረጃ በመስጠት ልንተባበር እንችላለን የሚለው ሀሳብም ሌላኛው በዚህ ሚስጢራዊ ቅጂ ላይ የተገኘው መረጃ ነው፡፡
ብሪታንያ ስቶርም ሻዶው የተባለውን ሚሳኤል ለዩክሬን በመስጠቷ የተወሰኑ ወታደሮቿ በዩክሬን ናቸው የሚሉ ሀሳቦችም በጀርመን የአየር ሀይል አመራሮች መነሳታቸውም ተገልጿል፡፡
መረጃው ይፋ መደረጉን ተከትሎ የጀርመን ህግ አውጪ ምክር ቤት አባላት ጉዳዩ ትልቅ ችግር መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል፡፡
ጀርመን ለዩክሬን ታውረስ የተሰኘውን ሚሳኤል ለዩክሬን እንዳትሰጥ እና ጫና ለመፍጠር በሚል ሩሲያ የጀርመን አየር ሀይል ውይይትን ሳትጠልፍ እንዳልቀረችም እየተገለጸ ይገኛል፡፡
የጀርመን መራሄ መንግስት ሀገራቸው ታውረስ የተሰኘውን ሚሳኤል ለዩክሬን ለመስጠት እንዳልፈቀደች ከሰሞኑ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ እንዳሉት የጀርመን አየር ሀይል አመራሮች ውይይት ሩሲያ በዩክሬን ከአውሮፓዊያን ጋር እየተዋጋች ለመሆኗ ዋና ማስረጃ ሆናል ብለዋል፡፡