ፖለቲካ
ሩሲያ የአየር ክልሏ በአሜሪካ መጣሱን ተከትሎ ተዋጊ ጀቶችን አሰማርታ እንደነበር ተገለጸ
ምዕራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ማዕቀቦችንም ጥለዋል
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው የሩሲያ የጸረ- ኤርክራፍት ኃይል የአሜሪካ የስለላ ድሮኖችን በማስጠንቀቅ አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርጓል ብለዋል
ሩሲያ በትናንትናው እለት በጥቁር ባህር በኩል ያለው ድንበሯ በአሜሪካ ድሮኖች መጣሱን ተከትሎ ተዋጊ ጀቶችን አሰማርታ እንደነበር የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በቴሌግራም ገጹ ባወጣው መግለጫ ድሮኖቹ ክሪሚያ አቅራቢያ ታይተው እንደነበር እና ለስለላ አላማ ወደ ሩሲያ ድንበር እያመሩ ነበር ብሏል።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው የሩሲያ የጸረ- ኤርክራፍት ኃይል የአሜሪካ የስለላ ድሮኖችን በማስጠንቀቅ አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርጓል ብለዋል።
ሮይተርስ የዚህን ጉዳይ ትክክለኛነት ማጣራት እንደማይችል ገልጿል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ማወጇን ተከትሎ አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ችግር ውስጥ ገብቷል።
ምዕራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ማዕቀቦችንም ጥለዋል።
ምዕራባውያን ከማዕቀብ ባለፈም ዩክሬን ሩሲያን እንድትመክት በሚል ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለውበታል።
ሩሲያ ለምዕራባውያን ጫና ሸብረክ እንደማትል በተደጋጋሚ ገልጻለች።