11 ዩክሬን ጦር ክፍሎች የታጠቁት ልዩ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟንም ሩሲያ አስታውቃለች
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዩክሬን በፈፀመው የአየር ድብደባ በርካታ ቁጥር ያላቸው ለዩክሬን ሲዋጉ የነበሩ የውጭ ሀገራት ቅጥረኛ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮናሽንኮቭ በእለታዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፤ የሩሲያ አየር ኃይል ኢለማውን የጠበቀ ከፍተኛ የአየር ጥቃት በዩክሬኗ ዴንፕሮቴስኮቭ ክልል ፈጽሟል።
የአየር ጥቃቱ ዓለም አቀፍ ተዋጊችን የያዘ የዩክሬን ክፍለ ጦርን ኢላማ ያደረገ እንደነበረም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።
በአየር ጥቃቱም ከ80 በላይ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ቅጥረኛ ወታደሮችን መግደሉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተጨማሪም የተለያዩ እና በአይነታቸው ልዩ የሆኑ የ11 ክፍለ ጦር ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች መውደማቸውንም ነው የሩሲያ ጦር ቃል አቀባይ በመግለጫው ያስታወቀው።
ከተለያዩ ሀገራት ተውጣጡ የውጭ ሀገራት ዜጎችን በውስጡ የያዘው የኪቭ ዓለም አቀፍ ክፍለ ጦር ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ ነበር ፕሬዝዳንተ ቮሊድሚር ዘለንስኪ የተመሰረተው።
ሩሲያ በተለያዩ ጊዜያት በዩክሬን ውስጥ በወሰደቻቸወው እርምጃዎችም የውጭ ሀገራት ቅጥረኛ ወታደሮችን ጨምሮ ምእራባወያን ለዩክሬን የለገሱትን የጦር መሳሪያ በተለያዩ ጊዜያት ማውደሟን ማስታወቂያ ይታወሳል።
ሩሲያ በቅርቡ በኦዴሳ ወደብ በፈፀመችው ጥቃት ምዕራባውያን ለዩክሬን ያቀረቧቸውን የጦር መሳሪያዎች ያወደመ ነበር ብላለች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሐምሌ 16 በወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ አሜሪካ ሰራሽ "HIMARS" ሮኬቶችን ማውደሙን አስታውቋል።